Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 9:56 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

56 የሰው ልጅ የሰ​ውን ነፍስ ሊያ​ድን እንጂ ሊያ​ጠፋ አል​መ​ጣም። ወደ ሌላም መን​ደር ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

56 ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

56 ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

56 ከዚያም ተነሥተው ወደ ሌላ መንደር ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

56 የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም አለ። ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 9:56
16 Referencias Cruzadas  

ክፉ​ውን በመ​ል​ካም ሥራ ድል ንሣው እንጂ ክፉ​ውን በክፉ ድል አት​ን​ሣው።


እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


ዓለም በእ​ርሱ ይድን ዘንድ ነው እንጂ በዓ​ለም እን​ዲ​ፈ​ርድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ወደ​ዚህ ዓለም አል​ላ​ከ​ው​ምና።


ሌባ ግን ሊሰ​ር​ቅና ሊያ​ርድ፥ ሊያ​ጠ​ፋም ካል​ሆነ በቀር አይ​መ​ጣም፤ እኔ ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኙ፥ እጅ​ግም እን​ዲ​በ​ዛ​ላ​ቸው መጣሁ።


የሰው ልጅ የጠ​ፋ​ውን ሊፈ​ል​ግና ሊያ​ድን መጥ​ቶ​አ​ልና።”


“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


“ኀጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ፤” የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤


ቃሌን ሰምቶ የማ​ይ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እኔ የም​ፈ​ር​ድ​በት አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ዓለ​ምን ላድን እንጂ በዓ​ለም ልፈ​ር​ድ​በት አል​መ​ጣ​ሁ​ምና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ​ንስ ተው” አለ፤ ወዲ​ያ​ውም ጆሮ​ውን ዳስሶ አዳ​ነው።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤


እርሱ ግን ዘወር ብሎ፥ “ከምን መን​ፈስ እንደ ሆና​ችሁ አታ​ው​ቁም” ብሎ ገሠ​ጻ​ቸው።


ከዚህ በኋላ በመ​ን​ገድ ሲሄዱ አንድ ሰው፥ “መም​ህር፥ ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በት ልከ​ተ​ል​ህን?” አለው።


የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios