Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 17:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መሰ​ና​ክል ግድ ይመ​ጣል፤ ነገር ግን መሰ​ና​ክ​ልን ለሚ​ያ​መ​ጣት ሰው ወዮ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “ሰዎችን የሚያሰናክል መምጣቱ አይቀርም፤ ነገር ግን ለመሰናክሉ መምጣት ምክንያት ለሚሆን ወዮለት!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ “መሰናክል የግዱን ሳይመጣ አይቀርም፤ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “ሰዎችን አሰናክለው ወደ ኃጢአት የሚጥሉ ነገሮች መምጣታቸው አይቀርም፤ ነገር ግን የኃጢአትን መሰናክል ለሚያመጣው ለዚያ ሰው ወዮለት!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፤

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 17:1
14 Referencias Cruzadas  

“ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፤ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት!


ነገር ግን በመ​ብል ምክ​ን​ያት ወን​ድሜ የሚ​ሰ​ና​ከል ከሆነ ወን​ድ​ሜን እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥጋን አል​በ​ላም።


እን​ግ​ዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በር​ሳ​ችን አን​ነ​ቃ​ቀፍ፤ ይል​ቁ​ንም ለወ​ን​ድም እን​ቅ​ፋ​ትን ወይም ማሰ​ና​ከ​ያን ማንም እን​ዳ​ያ​ኖር ይህን ዐስቡ።


ከእ​ና​ንተ የተ​መ​ረ​ጡት ወን​ድ​ሞች ተለ​ይ​ተው እን​ዲ​ታ​ወቁ ትለ​ያዩ ዘንድ ግድ ነው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እና​ንተ የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን ትም​ህ​ርት የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትን፥ መለ​ያ​የ​ት​ንና ማሰ​ና​ከ​ያን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን እን​ድ​ታ​ው​ቁ​ባ​ቸው እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤


እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፤ አንተ ሰይጣን! የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና፥ ዕንቅፋት ሆነህብኛል፤” አለው።


ለአ​ይ​ሁ​ድም፥ ለአ​ረ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ያለ ማሰ​ና​ከል አር​አያ ሁኑ​አ​ቸው።


ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።


ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤


አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴ​ንና ነቢ​ያ​ትን ካል​ሰ​ሙማ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነሣ ቢኖ​ርም እንኳ አይ​ሰ​ሙ​ትም፤ አያ​ም​ኑ​ት​ምም’ አለው።”


መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios