Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 16:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በዐ​መፃ ገን​ዘብ ካል​ታ​መ​ና​ችሁ በእ​ው​ነ​ተ​ኛው ገን​ዘብ ማን ያም​ና​ች​ኋል?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንግዲህ፣ በዚህ ዓለም ሀብት ካልታመናችሁ፣ እውነተኛውንማ ሀብት ማን ዐደራ ብሎ ይሰጣችኋል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንግዲያስ በዐመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ታዲያ የዚህን ዓለም ሀብት በማስተዳደር የማትታመኑ ከሆናችሁ እውነተኛውን ሀብትማ ማን አምኖ ይሰጣችኋል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል?

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 16:11
9 Referencias Cruzadas  

ሀብ​ታ​ች​ሁን ሸጣ​ችሁ ምጽ​ዋት ስጡ፤ ሌባ በማ​ያ​ገ​ኝ​በት ነቀ​ዝም በማ​ያ​በ​ላ​ሽ​በት፥ የማ​ያ​ረጅ ከረ​ጢት፥ የማ​ያ​ል​ቅም መዝ​ገብ በሰ​ማ​ያት ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ለማ​ንስ ለእኔ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ባለ​ጸ​ግ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ አስ​ተ​ምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ሰምቶ እን​ዲህ አለው፥ “አን​ዲት ቀር​ታ​ሃ​ለች፤ ሂድና ያለ​ህን ሁሉ ሸጠህ ለነ​ዳ​ያን ስጥ፤ በሰ​ማ​ይም መዝ​ገብ ታገ​ኛ​ለህ፤ መጥ​ተ​ህም ተከ​ተ​ለኝ።”


እኔም እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ባለ​ቀ​ባ​ችሁ ጊዜ እነ​ርሱ በዘ​ለ​ዓ​ለም ቤታ​ቸው ይቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ዘንድ በዐ​መፃ ገን​ዘብ ለእ​ና​ንተ ወዳ​ጆች አድ​ር​ጉ​በት።


ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።


“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።


በሌ​ላ​ውስ ገን​ዘብ ካል​ታ​መ​ና​ችሁ የራ​ሱን ማን ይሰ​ጣ​ች​ኋል?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios