Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 10:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 አንድ ሳም​ራዊ ግን በዚ​ያች መን​ገድ ሲሄድ አገ​ኘው፤ አይ​ቶም አዘ​ነ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 አንድ ሳምራዊ ግን እግረ መንገዱን ሲሄድ ሰውየው ወዳለበት ቦታ ደረሰ፤ ባየውም ጊዜ ዐዘነለት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 አንድ ሳምራዊ ግን በጉዞ ላይ ሳለ እርሱ ወደ ነበረበት መጣ አይቶትም አዘነለት፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 አንድ ሳምራዊ ግን በዚያ በኩል ሲያልፍ ወደ ሰውየው መጣ፤ ባየውም ጊዜ ራራለት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 10:33
14 Referencias Cruzadas  

አን​ተ​ንም የበ​ደ​ሉ​ህን ሕዝ​ብ​ህን ፥ በአ​ን​ተም ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን በደ​ላ​ቸ​ውን ሁሉ ይቅር በል፤ ይራ​ሩ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ በማ​ረ​ኩ​አ​ቸው ፊት ምሕ​ረ​ትን ስጣ​ቸው፤


ጌታ​ች​ንም በአ​ያት ጊዜ አዘ​ነ​ላ​ትና፥ “አታ​ል​ቅሺ” አላት።


እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን?’ አለው።


እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፤ አዘዛቸውም፤ እንዲህም አለ “በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፤ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት።


ያቺ የሰ​ማ​ርያ ሴትም፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን፥ እኔም ሳም​ራ​ዊት ስሆን እን​ዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልት​ጠጣ ትለ​ም​ና​ለህ?” አለ​ችው፤ አይ​ሁድ ከሳ​ም​ራ​ው​ያን ጋር በሥ​ር​ዐት አይ​ተ​ባ​በ​ሩም ነበ​ርና።


ሣጥ​ኑን በከ​ፈ​ተ​ችም ጊዜ ሕፃ​ኑን አየች፤ እነ​ሆም፥ ሕፃኑ በሣ​ጥኑ ውስጥ ያለ​ቅስ ነበር፤ የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ አዘ​ነ​ች​ለት፥ “ይህ ሕፃን ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።


እን​ዲ​ሁም አንድ ሌዋዊ በዚያ ቦታ አገ​ኘ​ውና፥ አይቶ እንደ ፊተ​ኛው አል​ፎት ሄደ።


ወደ እር​ሱም ቀረበ፤ ቍስ​ሉ​ንም አጋ​ጥሞ አሰ​ረ​ለት፤ በቍ​ስሉ ላይም ወይ​ንና ዘይት ጨመ​ረ​ለት፤ በአ​ህ​ያ​ውም ላይ አስ​ቀ​ምጦ እን​ዲ​ፈ​ው​ሰው የእ​ን​ግ​ዶ​ችን ቤት ወደ​ሚ​ጠ​ብ​ቀው ወሰ​ደው፤ የሚ​ድ​ን​በ​ት​ንም ዐሰበ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios