Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የም​ድ​ርም ሰን​በት ለአ​ንተ፥ ለወ​ንድ ባሪ​ያ​ህም፥ ለሴት ባሪ​ያ​ህም፥ ለም​ን​ደ​ኛም፥ ከአ​ንተ ጋር ለሚ​ኖር ለመ​ጻ​ተ​ኛም ምግብ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ምድሪቱም በሰንበት ጊዜዋ የምታስገኘው ማንኛውም ፍሬ ለአንተ፣ ለወንድ ባሪያህ፣ ለሴት ባሪያህ፣ ለቅጥር ሠራተኛህና ከአንተ ጋራ ለሚኖር መጻተኛ ምግብ ይሁን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የምድሪቱ ሰንበት ለእናንተ፥ ለአንተም፥ ለወንድ ባርያህም፥ ለሴት ባርያህም፥ ተቀጥሮ ለሚያገለግልህም፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ለመጻተኛም ምግብ ትሰጣችኋለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በምድር ሰንበት ዓመት የሚበቅለው ሰብል ሁሉ ለአንተ፥ ለወንድ አገልጋይህ፥ ለሴት አገልጋይህ፥ ለቅጥረኛህ፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ጊዜያዊ መጻተኛ ምግብ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የምድርም ሰንበት ለአንተ፥ ለወንድ ባሪያህም፥ ለሴት ባሪያህም፥ ለምንደኛም፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ለመጻተኛም ምግብ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 25:6
9 Referencias Cruzadas  

“ይህም ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በዚህ ዓመት የገ​ቦ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ለህ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ለህ፤ ታጭ​ድ​ማ​ለህ፥ ወይ​ንም ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ለህ።


በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳ​ር​ፋ​ትም፤ የሕ​ዝ​ብ​ህም ድሆች ይበ​ሉ​ታል፤ እነ​ርሱ ያስ​ቀ​ሩ​ት​ንም የሜዳ እን​ስሳ ይብ​ላው። እን​ዲ​ሁም በወ​ይ​ን​ህና በወ​ይ​ራህ አድ​ርግ።


እና​ን​ተም፦ ‘ካል​ዘ​ራን፥ እህ​ላ​ች​ን​ንም ካላ​ከ​ማ​ቸን በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ምን እን​በ​ላ​ለን?’ ብትሉ፥


እኔ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በረ​ከ​ቴን በላ​ያ​ችሁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም የሦ​ስት ዓመት ፍሬ ታፈ​ራ​ለች።


የም​ድ​ራ​ች​ሁን ገቦ አት​ጨ​ደው፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የወ​ይ​ን​ህን ፍሬ አታ​ከ​ማች፤ ለም​ድ​ሪቱ የዕ​ረ​ፍት ዓመት ይሆ​ናል።


ለእ​ን​ስ​ሶ​ች​ህም፥ በም​ድ​ር​ህም ላሉት አራ​ዊት ፍሬዋ ሁሉ ምግብ ይሁን።


ያመ​ኑ​ትም ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ይኖሩ ነበር፤ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ነበር።


ያመ​ኑ​ትም ሁሉ አንድ ልብና አን​ዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሁሉ ገን​ዘብ በአ​ን​ድ​ነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገን​ዘብ ነው” የሚል አል​ነ​በ​ረም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos