Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 18:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እና​ን​ተም የሀ​ገሩ ልጆች፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል የሚ​ኖ​ሩት እን​ግ​ዶች ከዚህ ርኵ​ሰት ምንም አት​ሥሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እናንተ ግን ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እናንተ የአገር ተወላጆችና በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም አትፈጽሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፤ እናንተም የአገሩም ተወላጅ በእናንተም መካከል የሚኖር እንግዳ ርኩሰት ከሆኑት ከእነዚህ ማናቸውንም ነገር አታድርጉ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ትእዛዞቼንና ኅጎቼን ጠብቁ፤ ከእነዚህ ርኲሰቶች እናንተም ሆናችሁ በመካከላችሁ የሚኖሩ ባዕዳን አንዳቸውንም አታድርጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፤ እናንተም የአገሩ ልጆች በእናንተም መካከል የሚኖሩት እንግዶች ከዚህ ርኵሰት ምንም አትሥሩ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 18:26
16 Referencias Cruzadas  

የሚ​ሠ​ራ​ቸው ሰው በእ​ነ​ርሱ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልና ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


እና​ን​ተስ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ ካደ​ረ​ጋ​ችሁ ወዳ​ጆች ናችሁ።


“ከወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ኝስ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ።


እር​ሱም፥ “ብፁ​ዓ​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ጠ​ብቁ ናቸው” አላት።


በመ​ል​ካም ምድር የወ​ደ​ቀው ግን ቃሉን በበ​ጎና በን​ጹሕ ልብ የሚ​ሰ​ሙና የሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ ታግ​ሠ​ውና ጨክ​ነ​ውም የሚ​ያ​ፈሩ ናቸው።


“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ሁሉ ታደ​ር​ገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእ​ርሱ ላይ አት​ጨ​ምር፤ ከእ​ር​ሱም ምንም አታ​ጕ​ድል።


ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”


ስለ​ዚህ ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በሩ ሰዎች የሠ​ሩ​ትን ጸያፍ የሆ​ነ​ውን ወግ ሁሉ እን​ዳ​ት​ሠሩ፥ በእ​ር​ሱም እን​ዳ​ት​ረ​ክሱ ሥር​ዐ​ቴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”


“ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚ​በ​ላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ያንም ሰው ከሕ​ዝቡ ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


ለእ​ነ​ርሱ እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ሌላ መሥ​ዋ​ዕት ቢያ​ቀ​ርብ፥


ምድ​ሪ​ቱም ረከ​ሰች፤ ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ቷን በእ​ር​ስዋ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትን ሰዎች ትተ​ፋ​ለች።


ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በ​ሩት የሀ​ገሩ ልጆች ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ታ​ልና፤


በም​ድ​ርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ደ​ዳ​ቸው የአ​ሕ​ዛ​ብን ርኵ​ሰት ሁሉ ያደ​ርጉ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios