Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 16:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ይህም አንድ ጊዜ በዓ​መት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 “ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሁናችሁ፤ በዚህም ሥርዐት መሠረት ለእስራኤላውያን ኀጢአት ሁሉ በዓመት አንድ ጊዜ ስርየት ይደረግ።” እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ተደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ይህም አንድ ጊዜ በዓመት ለእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸው ሁሉ ለማስተሰረይ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆንላችኋል።” ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 በዓመት አንድ ጊዜ የእስራኤላውያንን ኃጢአት ሁሉ ማስተስረይ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።” በዚህም ዐይነት ሙሴ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ይህም አንድ ጊዜ በዓመት ለእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸው ሁሉ ያስተሰርይ ዘንድ የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 16:34
14 Referencias Cruzadas  

በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።


አሮ​ንም በዓ​መት አንድ ጊዜ በቀ​ን​ዶቹ ላይ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ር​ጋል፤ በዓ​መት አንድ ጊዜ ኀጢ​አ​ትን ከሚ​ያ​ነ​ጻው ደም ይወ​ስ​ዳል፤ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ነጻ ያደ​ር​ጋል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።”


ሙሴም ሥራ​ውን ሁሉ አየ፤ እነ​ሆም፥ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ ሙሴም ባረ​ካ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስ​ር​የቱ መክ​ደኛ ላይ በደ​መ​ናው ውስጥ እታ​ያ​ለ​ሁና እን​ዳ​ይ​ሞት በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ወዳ​ለው ወደ ስር​የቱ መክ​ደኛ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ሁል​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ገባ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን ንገ​ረው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው-


በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እና​ንተ ማስ​ተ​ስ​ረያ ትሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ የማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን ናትና በዚ​ያች ቀን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት።


ሥራ ሁሉ አታ​ድ​ር​ጉ​ባት፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ነው።


ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ተሳ​ዳ​ቢ​ው​ንም ከሰ​ፈር ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩት። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።


ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”


“የዚ​ህም ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቁ​አት፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታ​ድ​ርጉ።


ለሚ​ቀ​ደ​ሱ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ት​ሆን አን​ዲት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ።


ነገር ግን በዚ​ያው መሥ​ዋ​ዕት በየ​ዓ​መቱ የኀ​ጢ​አት መታ​ሰ​ቢያ አድ​ር​ገው የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ነበ​ራ​ቸው።


ሊቀ ካህ​ናቱ ያደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ በያ​መ​ቱም ደም ይዞ ወደ ቅድ​ስት ይገባ እንደ ነበረ ዘወ​ትር ራሱን የሚ​ሠዋ አይ​ደ​ለም።


ወደ ሁለ​ተ​ኛ​ዪቱ ክፍል ግን ሊቀ ካህ​ናቱ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ደም ይዞ፥ በየ​ዓ​መቱ አንድ ጊዜ ብቻ​ውን ይገባ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos