Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 16:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “አሮ​ንም ስለ ራሱ ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ያቀ​ር​ባል፤ ለራ​ሱም ለቤ​ተ​ሰ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ስለ ኀጢ​አቱ የእ​ር​ሱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ያር​ዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “አሮን ለራሱና ለቤተ ሰቡ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ወይፈኑን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ስለ ራሱ ያቅርብ፤ ወይፈኑንም ስለ ራሱ የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ይረድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “አሮንም ለእርሱ የሆነውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያቀርባል፤ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል፤ ለእርሱ የሆነውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያርዳል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አሮንም ኰርማውን ስለ ራሱና ስለ ቤተሰቡ የኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት በማድረግ ይረደው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አሮንም ስለ ራሱ ኃጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት ወይፈኑን ያቀርባል፤ ለራሱም ለቤተ ሰቡም ያስተሰርያል፤ ስለ ኃጢአቱ የእርሱን መሥዋዕት ወይፈኑን ያርዳል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 16:11
6 Referencias Cruzadas  

እን​ዲሁ አሮን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች ወይ​ፈን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ይግባ።


ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ንም ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን፥ ለመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ ለካ​ህ​ና​ቱም፥ ለጉ​ባ​ኤ​ውም ሕዝብ ሁሉ ያስ​ተ​ስ​ርይ።


“አሮ​ንም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን ያቀ​ር​ባል፤ ለራ​ሱም፥ ለቤ​ተ​ሰ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ወደ መሠ​ዊ​ያው ቀር​በህ የኀ​ጢ​አ​ት​ህን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን ሠዋ፤ ለራ​ስ​ህና ለወ​ገ​ንህ አስ​ተ​ስ​ርይ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘዘ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቅ​ርብ፤ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላ​ቸ​ውም” አለው።


እር​ሱም እንደ እነ​ዚያ ሊቃነ ካህ​ናት አስ​ቀ​ድሞ ስለ ራሱ ኀጢ​አት በኋ​ላም ስለ ሕዝቡ ኀጢ​አት ዕለት ዕለት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ አያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውም፤ ራሱን ባቀ​ረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።


ወደ ሁለ​ተ​ኛ​ዪቱ ክፍል ግን ሊቀ ካህ​ናቱ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ደም ይዞ፥ በየ​ዓ​መቱ አንድ ጊዜ ብቻ​ውን ይገባ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos