Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 15:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እነ​ዚ​ህ​ንም ነገ​ሮች የሚ​ነካ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ልብ​ሱ​ንም ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እነዚህንም የሚነካ ማንኛውም ሰው ርኩስ ይሆናል፤ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እነዚህንም ነገሮች የሚነካ ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እነርሱንም የሚነካ ሁሉ ስለሚረክስ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱን ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እነዚህንም ነገሮች የሚነካ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ልብሱንም ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 15:27
15 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።


እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።


ነውር የሌ​ለው ሆኖ፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ፈስ ራሱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረበ የክ​ር​ስ​ቶስ ደም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ከው ዘንድ ሕሊ​ና​ች​ንን ከሞት ሥራ እን​ዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


ከር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እህ​ል​ንም እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ው​ማ​ለሁ፤ ራብ​ንም አላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም።


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


መኝ​ታ​ዋ​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ልብ​ሶ​ቹን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ሰው​ነ​ቱን ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


“ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው ከፈ​ሳሹ ነገር ሲነጻ ስለ መን​ጻቱ ሰባት ቀን ይቈ​ጥ​ራል፤ ልብ​ሶ​ቹ​ንም ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በም​ንጭ ውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።


ደም​ዋም በሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ወራት ሁሉ የም​ት​ተ​ኛ​በት መኝታ ሁሉ በግ​ዳ​ጅዋ ጊዜ እንደ ነበ​ረው መኝታ ያለ ይሆ​ን​ባ​ታል፤ የም​ት​ቀ​መ​ጥ​በት ነገር ሁሉ እንደ ግዳ​ጅዋ ርኩ​ስ​ነት ርኩስ ነው።


ከፈ​ሳ​ሽ​ዋም ብት​ነጻ ሰባት ቀን ትቈ​ጥ​ራ​ለች፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጽ​ሕት ትሆ​ና​ለች።


“በእ​ነ​ዚ​ህም ርኩስ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ የእ​ነ​ር​ሱ​ንም በድን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ርኩ​ሱም የሚ​ነ​ካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆ​ናል፤ የሚ​ነ​ካ​ውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios