Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ያል​ታ​ረ​ደ​ች​ው​ንም ዶሮ፥ ዝግ​ባ​ው​ንም ዕን​ጨት፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ሂሶ​ጱ​ንም ወስዶ በም​ንጭ ውኃ ላይ በታ​ረ​ደ​ችው ዶሮ ደም ውስጥ ይነ​ክ​ራ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በሕይወት ያለውንም ወፍ ከዝግባው ዕንጨት፣ ደመቅ ካለው ቀይ ድርና ከሂሶጵ ጋራ በምንጩ ውሃ ላይ በታረደው ወፍ ደም ውስጥ ይንከር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በሕይወት ያለውን ወፍ፥ የዝግባውንም እንጨት፥ ቀዩንም ግምጃ፥ ሂሶጱንም ወስዶ ይነክራቸዋል፥ በሕይወትም ያለውን ወፍ በምንጭ ውኃ ላይ በታረደው የወፍ ደም ውስጥ ይዘፍቀዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሌላውንም ወፍ ወስዶ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ቊራጭ፥ ከቀዩ ከፈይ ክርና ከሂሶጱ ቅጠል ጋር በአንድነት ቀድሞ በታረደው ወፍ ደም ውስጥ ይንከረው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሕያውንም ወፍ ዝግባውንም እንጨት ቀዩንም ግምጃ ሂሶጱንም ወስዶ ከሕያው ወፍ ጋር በምንጭ ውኃ ላይ በታረደው ወፍ ደም ውስጥ ይነክራቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 14:6
13 Referencias Cruzadas  

“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥ በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”


እነ​ሆም፥ የለ​ምጹ ደዌ ከለ​ም​ጻሙ ላይ ቢጠፋ፥ ካህኑ ስለ​ሚ​ነ​ጻው ሰው ሁለት ንጹ​ሓን ዶሮ​ዎች በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው፥ የዝ​ግ​ባም ዕን​ጨት፥ ቀይ ግም​ጃም፥ ሂሶ​ጵም ያመጣ ዘንድ ያዝ​ዛል።


ካህ​ኑም ከሁ​ለቱ ዶሮ​ዎች አን​ደ​ኛ​ዋን በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ በም​ንጭ ውኃ ላይ ያርድ ዘንድ ያዝ​ዛል።


አን​ደ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ዶሮ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ከም​ንጩ ውኃ በላይ ያር​ዳል።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


ገና ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ዓለም አያ​የ​ኝም፤ እና​ንተ ግን ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እና​ን​ተም ሕያ​ዋን ትሆ​ና​ላ​ችሁ።


እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቹ ስን​ሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታ​ረ​ቀን በኋ​ላም በልጁ ሕይ​ወት እን​ዴት የበ​ለጠ ያድ​ነን!


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


ሕያውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበርሁ፤ እነሆም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos