Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 14:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 “ካህ​ኑም ገብቶ ቢያ​የው፥ እነ​ሆም፥ ቤቱ ከተ​መ​ረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይ​ሰፋ፥ ደዌው ስለ ሻረ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 “ነገር ግን ቤቱ ከተመረገ በኋላ፣ ካህኑ ሊመረምረው በሚመጣበት ጊዜ ተላላፊው በሽታ ሳይስፋፋ ቢገኝ፣ በሽታው ስለ ለቀቀው ቤቱ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 “ካህኑም ገብቶ ቢያይ፥ እነሆም፥ ቤቱ ከተመረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይሰፋ፥ ደዌው ስለ ጠፋ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 “ቤቱ እንደገና ታድሶ ከተለሰነ በኋላ ካህኑ መጥቶ በሚመለከትበት ጊዜ ሻጋታው የመስፋፋት ምልክት የማያሳይ ሆኖ ከተገኘ ግን የሻጋታው ምልክት ጨርሶ ስለ ጠፋ ያ ቤት ንጹሕ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 ካህኑም ገብቶ ቢያይ፥ እነሆም፥ ቤቱ ከተመረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይሰፋ፥ ደዌው ስለ ሻረ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 14:48
10 Referencias Cruzadas  

እን​ግ​ዲህ እና​ንተ እን​ዲህ ስት​ሆኑ እነ​ማን ናችሁ? ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም መን​ፈስ ታጥ​ባ​ች​ኋል፤ ተቀ​ድ​ሳ​ች​ኋል፤ ጸድ​ቃ​ች​ኋ​ልም።


ያን​ጊ​ዜም ብዙ​ዎ​ችን ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውና ከሕ​መ​ማ​ቸው ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ን​ትም ፈወ​ሳ​ቸው፤ ለብ​ዙ​ዎች ዕው​ራ​ንም እን​ዲ​ያዩ ብር​ሃ​ንን ሰጣ​ቸው።


እርሱም “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሽ፤” አላት።


ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ፤ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች።


በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ በማ​ለዳ ወደ እኔ ይገ​ሰ​ግ​ሳሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​መ​ለስ፤ እርሱ ሰብ​ሮ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይፈ​ው​ሰ​ናል፤ እርሱ መት​ቶ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይጠ​ግ​ነ​ናል።


እርሱ ይሰ​ብ​ራል፥ ዳግ​መ​ኛም ይጠ​ግ​ናል፤ ይቀ​ሥ​ፋል፥ እጆ​ቹም ይፈ​ው​ሳሉ።


ካህ​ኑም ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ይወ​ጣል፤ ካህ​ኑም ያየ​ዋል፤


“ደዌ​ውም ዳግም ቢመ​ለስ፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹም ከወጡ፥ ቤቱም ከተ​ፋ​ቀና ከተ​መ​ረገ በኋላ በቤቱ ውስጥ ቢሰፋ፥


በቤ​ቱም የሚ​ተኛ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ በቤ​ቱም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


ካህ​ኑም ቤቱን ለማ​ን​ጻት ሁለት ዶሮ​ዎች፥ የዝ​ግባ ዕን​ጨት፥ ቀይ ግምጃ፥ ሂሶ​ጵም ይወ​ስ​ዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios