Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 13:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 “ማና​ቸ​ውም ወንድ ወይም ሴት በራሱ ወይም በአ​ገጩ የለ​ምጽ ደዌ ቢኖ​ር​በት፥ ካህኑ የለ​ም​ጹን ደዌ ያያል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “በወንድ ወይም በሴት ዐናት ወይም አገጭ ላይ ቍስል ቢወጣ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 “ማናቸውም ወንድ ወይም ሴት በራስ ወይም በአገጭ ላይ ደዌ ቢኖርባቸው፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በራስ ወይም በአገጭ ላይ ቊስል ቢወጣበት ወይም ቢወጣባት፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ማናቸውም ወንድ ወይም ሴት በራሱ ወይም በአገጩ ደዌ ቢኖርበት፥

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 13:29
19 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ተማ​ከረ፤ ሁለ​ትም የወ​ርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መው​ጣት ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡ​አ​ችሁ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ እነሆ” አላ​ቸው።


ማና​ቸ​ውም ሰው የል​ቡን ሕመም ዐውቆ ጸሎ​ትና ምህላ ቢያ​ደ​ርግ፥ እጆ​ቹ​ንም ወደ​ዚህ ቤት ቢዘ​ረጋ፥


ማንም ሰው ወይም ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ማና​ቸ​ውም ሰው ሕማ​ሙ​ንና ኀዘ​ኑን ዐውቆ ጸሎ​ትና ልመና ቢያ​ደ​ርግ፥ እጆ​ቹ​ንም ወደ​ዚህ ቤት ቢዘ​ረጋ፥


ይህ​ንም ነገር በሰ​ማሁ ጊዜ ልብ​ሴ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዬን ቀደ​ድሁ፤ አዘ​ን​ሁም፤ የራ​ሴ​ንና የጢ​ሜ​ንም ጠጕር ነጨሁ፤ ደን​ግ​ጬም ተቀ​መ​ጥሁ።


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፥ ጌታ​ዬም ነፍ​ሴን ያድ​ና​ታል።


እን​ግ​ዲህ በበ​ደል ላይ በደል እየ​ጨ​መ​ራ​ችሁ ለምን ትቀ​ሠ​ፋ​ላ​ችሁ? ራስ ሁሉ ለሕ​ማም፥ ልብም ሁሉ ለኀ​ዘን ሆኖ​አል።


ክፉ​ውን መል​ካም መል​ካ​ሙ​ንም ክፉ ለሚሉ፥ ጨለ​ማ​ውን ብር​ሃን ብር​ሃ​ኑ​ንም ጨለማ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ ጣፋ​ጩን መራራ መራ​ራ​ው​ንም ጣፋጭ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ወዮ​ላ​ቸው!


ሽማ​ግ​ሌ​ውና ለፊት የሚ​ያ​ደ​ላው እርሱ ራስ ነው፤ ዐመ​ፅ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ራስን ከሚ​ላጭ ምላጭ ይልቅ የተ​ሳለ ጐራ​ዴን ውሰድ፤ ወስ​ደ​ህም በእ​ር​ስዋ ራስ​ህ​ንና ጢም​ህን ተላጭ፤ ሚዛ​ን​ንም ውሰድ፤ ጠጕ​ሩ​ንም ትከ​ፋ​ፍ​ለ​ዋ​ለህ።


ቋቍ​ቻ​ውም በስ​ፍ​ራው ላይ ቢቆም፥ በቆ​ዳ​ውም ላይ ባይ​ሰፋ፥ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ የት​ኩ​ሳት እባጭ ነው፤ የት​ኩ​ሳ​ትም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል።


እነ​ሆም፥ ወደ ቆዳው ቢጠ​ልቅ፥ በው​ስ​ጡም ቀጭን ብጫ ጠጕር ቢኖ​ር​በት፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ ቈረ​ቈር ነው፤ የራስ ወይም የአ​ገጭ ለምጽ ነው።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።


ዐይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos