Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሰቈቃወ 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ኖን። እነ​ርሱ ታው​ረው በመ​ን​ገድ ላይ ተቅ​በ​ዘ​በዙ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ዳ​ሰስ በደም ረክ​ሰ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንደ ታወሩ ሰዎች፣ በየመንገዱ ላይ ይደናበራሉ፤ ማንም ሰው ደፍሮ ልብሳቸውን መንካት እስከማይችል ድረስ፣ በደም እጅግ ረክሰዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ኖን። ታውረው በመንገድ ላይ ተቅበዘበዙ፥ ልብሳቸው እንዳይዳሰስ በደም ረክሰዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እነርሱ በደም የረከሱ ስለ ሆኑ ሰው ልብሳቸውን እንኳ ለመንካት አይደፍርም፤ እነርሱ ግን እንደ ዕውሮች በመንገድ ላይ ይንከራተታሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ኖን። ታውረው በመንገድ ላይ ተቅበዘበዙ፥ ልብሳቸው እንዳይዳሰስ በደም ረክሰዋል።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 4:14
15 Referencias Cruzadas  

እጃ​ች​ሁን ወደ እኔ ብት​ዘ​ረጉ፥ ዐይ​ኖ​ችን ከእ​ና​ንተ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምህ​ላ​ንም ብታ​በዙ አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጆ​ቻ​ችሁ ደምን ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።


ሁሉም ዕው​ራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕው​ቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮ​ኹም ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ማን​ቀ​ላ​ፋ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳሉ።


በእ​ጆ​ች​ሽም የን​ጹ​ሓን ድሆች ደም ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግ​ልጥ አገ​ኘ​ሁት እንጂ በጕ​ድ​ጓድ ፈልጌ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም።


ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ይና​ገር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ በፈ​ጸመ ጊዜ ካህ​ና​ትና ነቢ​ያተ ሐሰት፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ሞትን ትሞ​ታ​ለህ” ብለው ያዙት።


ሴቶቹ አመ​ን​ዝ​ሮች ናቸ​ውና፥ በእ​ጃ​ቸ​ውም ደም አለና ጻድ​ቃን ሰዎች በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ቹና በደም አፍ​ሳ​ሾቹ ሴቶች ላይ በሚ​ፈ​ረ​ደው ፍርድ ይፈ​ር​ዱ​ባ​ቸ​ዋል።”


ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ።


በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፣ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።


በሜ​ዳም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን ወይም የሞ​ተ​ውን በድን፥ ወይም የሰ​ውን አጥ​ንት፥ ወይም መቃ​ብር የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


ምድ​ርን የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳት ደም ነውና የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን ምድር በነ​ፍስ ግድያ አታ​ር​ክ​ሷት። ምድ​ሪ​ቱም በደም አፍ​ሳሹ ደም ካል​ሆነ በቀር ከፈ​ሰ​ሰ​ባት ደም አት​ነ​ጻም።


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ።


ልቡ​ና​ቸው የተ​ጨ​ፈነ ነው፤ በስ​ን​ፍ​ና​ቸ​ውና በድ​ን​ቍ​ር​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጣ​ቸው ሕይ​ወት የተ​ለዩ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos