Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ዮዲት 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እነርሱም ወደ እርስዋ መጡ፤ እርስዋም “ዛሬ በሕዝቡ ፊት የተናገራችሁት በጎ ነገር አይደለምና በቤጤልዋ የሚኖሩ ሰዎች ሹሞች ሆይ! ስሙኝ እግዚአብሔር በእነዚህ በአምስቱ ቀኖች ባይረዳችሁ ሀገራችሁን ለጠላቶቻችሁ አሳልፋችሁ ትሰጡ ዘንድ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል የተማማላችሁትን መሐላ በዚህ አጸናችሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 እነርሱም ወደ እርሷ መጡ፥ እርሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “የቤቱሊያ ነዋሪዎች ገዢዎች ሆይ ስሙኝ! በዚህ ቀን በሕዝቡ ፊት የተናገራችሁት ንግግር ልክ አይደለም፤ በእግዚብአብሔርና በእናንተ መካከልም ይህን መሐላ አቆማችሁ፥ ጌታ ባይረዳችሁ ከተማይቱን ለጠላቶቻችን አሳልፋችሁ እንደምትሰጡ ተናገራችሁ። Ver Capítulo |