Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በሐ​ናት ልጅ በሰ​ሜ​ጋር ዘመን፥ በኢ​ያ​ዔል ዘመን ነገ​ሥት መን​ገ​ዶ​ችን ተዉ፤ በስ​ርጥ መን​ገ​ድም ይሄዱ ነበር፤ በጠ​ማማ መን​ገ​ድም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣ በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዓናት ልጅ በሻምጋር ዘመን፥ በያዔል ዘመን መንገዶች ተቋረጡ፥ መንገደኞች በስርጥ መንገድ ይሄዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዐናት ልጅ በሻምጋርና በያዔል ዘመን፥ የሲራራ ነጋዴዎች በምድሪቱ አያልፉም ነበር፤ መንገደኞችም ተደብቀው በዘወርዋራ መንገድ ይሄዱ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፥ በኢያዔል ዘመን መንገዶች ተቋረጡ፥ መንገደኞች በስርጥ መንገድ ይሄዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 5:6
11 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ዘመን ለሚ​ወ​ጣ​ውና ለሚ​ገ​ባው ሰላም አይ​ሆ​ን​ለ​ትም፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ላይ ታላቅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ይሆ​ናል።


በል​ቅሶ የሚ​ዘሩ በደ​ስታ ይሰ​በ​ስ​ባሉ።


መን​ገ​ዶች ባድማ ሆኑ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም መፈ​ራት ቀረ፤ ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውም ፈረሰ፤ እንደ ሰውም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸ​ውም።


የጠ​ላት ሰይፍ ከብ​በ​ዋ​ች​ኋ​ልና ወደ ሜዳ አት​ውጡ፤ በመ​ን​ገ​ድም ላይ አት​ሂዱ።


ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚ​መጣ የለ​ምና የጽ​ዮን መን​ገ​ዶች አለ​ቀሱ፤ በሮ​ችዋ ሁሉ ፈር​ሰ​ዋል፤ ካህ​ና​ቷም ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ደና​ግ​ሎ​ች​ዋም ተማ​ረኩ፤ እር​ስ​ዋም በም​ሬት አለች።


ጻዴ። ልጆ​ቻ​ች​ንን ወደ አደ​ባ​ባ​ያ​ችን እን​ዳ​ይ​ወጡ ከለ​ከ​ልን፤ የም​ን​ጠ​ፋ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ዘመ​ና​ችን አለቀ፤ የም​ን​ጠ​ፋ​በ​ትም ጊዜ ቀረበ።


በእ​ና​ንተ ላይ ክፉ​ዎች የም​ድ​ርን አራ​ዊት እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ይበ​ሉ​አ​ች​ኋል፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ያጠ​ፋሉ፤ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ን​ሳሉ፤ መን​ገ​ዶ​ቻ​ች​ሁም በረሃ ይሆ​ናሉ።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የሐ​ናት ልጅ ሴሜ​ጋር ተነሣ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ስድ​ስት መቶ ሰው በበሬ መው​ጊያ ገደለ፤ እር​ሱም ደግሞ እስ​ራ​ኤ​ልን አዳነ።


መተ​ር​ጕ​ማን ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አለቁ፥ ዲቦራ እስ​ክ​ት​ነሣ ድረስ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እናት ሆና እስ​ክ​ት​ነሣ ድረስ አለቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos