Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ተመ​ል​ከ​ቱም፤ እነሆ፥ የሴሎ ሴቶች ልጆች አታሞ ይዘው ለዘ​ፈን ሲወጡ ከወ​ይኑ ስፍራ ውጡ፤ ከሴሎ ሴቶች ልጆ​ችም ለየ​ራ​ሳ​ችሁ ሚስ​ትን ንጠቁ፤ ወደ ብን​ያም ምድ​ርም ሂዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አድፍጣችሁ ተጠባበቁ። የሴሎ ልጃገረዶች ለጭፈራ ወደዚያ በሚወጡበት ጊዜ፣ ከወይኑ አትክልት ቦታ ወጥታችሁ ከልጃገረዶቹ ለየራሳችሁ ሚስት ጥለፉ፤ ወደ ብንያምም ምድር ሂዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አድፍጣችሁ ተጠባበቁ። የሴሎ ልጃገረዶች ለጭፈራ ወደዚያ በሚወጡበት ጊዜ፥ ከወይኑ አትክልት ቦታ ወጥታችሁ ከልጃገረዶቹ ለየራሳችሁ ሚስት ጥለፉ፤ ወደ ብንያምም ምድር ሂዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ተጠባበቁ፤ በበዓሉ ዕለት የሴሎ ልጃገረዶች ለመጨፈር ሲመጡ እናንተም ከወይኑ ተክል ውስጥ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁ ከእነዚያ ልጃገረዶች መካከል እየጠለፋችሁ ሚስት አድርጋችሁ ውሰዱ፤ ወደ ብንያም ግዛትም ይዛችኋቸው ሂዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ተመልከቱም፥ እነሆም፥ የሴሎ ሴቶች ልጆች አታሞ ይዘው ለዘፈን ሲወጡ ከወይኑ ስፍራ ውጡ፥ ከሴሎም ሴቶች ልጆች ለየራሳችሁ ሚስት ንጠቁ፥ ወደ ብንያም ምድርም ሂዱ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 21:21
13 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በገና ይደ​ረ​ድር ነበር፤ ዳዊ​ትም ለዐ​ይን የሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ የሐር ቀሚስ ለብሶ ነበር።


ዳዊ​ትም ሜል​ኮ​ልን፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘም​ሬ​አ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአ​ባ​ት​ሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመ​ረ​ጠኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ይሁን፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጫ​ወ​ታ​ለሁ፤ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም፤


ስሙን በደ​ስታ ያመ​ሰ​ግ​ናሉ፥ በከ​በ​ሮና በበ​ገና ይዘ​ም​ሩ​ለ​ታል።


በከ​በ​ሮና በሽ​ብ​ሸባ አመ​ስ​ግ​ኑት፤ አው​ታር በአ​ለው መሣ​ሪ​ያና በእ​ን​ዚራ አመ​ስ​ግ​ኑት።


የአ​ሮን እኅት ነቢ​ይቱ ማር​ያ​ምም ከበሮ በእ​ጅዋ ወሰ​ደች፤ ሴቶ​ችም ሁሉ በከ​በ​ሮና በዝ​ማሬ በኋ​ላዋ ወጡ።


ለማ​ል​ቀስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሣ​ቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ዝ​ፈ​ንም ጊዜ አለው።


በዚያ ጡቶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፥ ሰው​ነ​ቴም አላ​ወ​ቀ​ችም፥ እንደ አሚ​ና​ዳብ ሰረ​ገላ አደ​ረ​ገኝ አለች።


በዚ​ያን ጊዜም ደና​ግሉ በዘ​ፈን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቱና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም በአ​ንድ ላይ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ እኔም ልቅ​ሶ​አ​ቸ​ውን ወደ ደስታ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከኀ​ዘ​ና​ቸ​ውም ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤


ነገር ግን ከዚህ ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ብዙ መከ​ራን ይቀ​በ​ላል፤ ይህች ትው​ል​ድም ትን​ቀ​ዋ​ለች፤ ትፈ​ታ​ተ​ነ​ዋ​ለ​ችም።


ዮፍ​ታ​ሔም ወደ መሴፋ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ልጁ ከበሮ ይዛ እየ​ዘ​ፈ​ነች ልት​ቀ​በ​ለው ወጣች፤ ለእ​ር​ሱም የሚ​ወ​ድ​ዳት አን​ዲት ብቻ ነበ​ረች። ከእ​ር​ስ​ዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አል​ነ​በ​ረ​ውም።


የብ​ን​ያ​ም​ንም ልጆች እን​ዲህ ብለው አዘ​ዙ​አ​ቸው፥ “ሂዱ በወ​ይ​ኑም ስፍራ ተደ​በቁ፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ገድሎ በተ​መ​ለሰ ጊዜ፥ እየ​ዘ​መ​ሩና እየ​ዘ​ፈኑ፥ እል​ልም እያሉ ከበ​ሮና አታሞ ይዘው ዳዊ​ትን ሊቀ​በሉ ሴቶች ከእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ሁሉ ወጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos