Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 11:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዮፍ​ታ​ሔም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ፊት ሸሽቶ በጦብ ምድር ተቀ​መጠ፤ ድሆች ሰዎ​ችም ተሰ​ብ​ስ​በው ዮፍ​ታ​ሔን ተከ​ተ​ሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህም ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ሸሽቶ መኖሪያውን ጦብ በተባለች ምድር አደረገ፤ እዚያም ወሮበሎች ተሰባስበው ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህም ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ሸሽቶ መኖሪያውን ጦብ በተባለች ምድር አደረገ፤ እዚያም ወሮበሎች ተሰባስበው ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዮፍታሔም ከወንድሞቹ ሸሽቶ ጦብ ተብላ በምትጠራ ምድር ኖረ፤ እዚያ ጥቂት ወሮበሎች ተሰብስበው ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዮፍታሔም ከወንድሞቹ ፊት ሸሽቶ በጦብ ምድር ተቀመጠ፥ ምናምንቴዎችም ሰዎች ተሰብስበው ዮፍታሔን ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 11:3
9 Referencias Cruzadas  

የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ወገ​ኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአ​ሞን ልጆች ልከው ከቤ​ት​ሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያ​ንና ከሱባ ሶር​ያ​ው​ያን ሃያ ሺህ እግ​ረ​ኞ​ችን፥ ከአ​ማ​ሌቅ ንጉ​ሥም አንድ ሺህ ሰዎ​ችን፥ ከአ​ስ​ጦ​ብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ቀጠሩ።


የአ​ሞ​ንም ልጆች ወጥ​ተው በበሩ መግ​ቢያ ፊት ለፊት ይዋጉ ጀመሩ፤ የሱ​ባና የሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያን፥ የአ​ስ​ጦ​ብና የአ​ማ​ሌ​ቅም ሰዎች ለብ​ቻ​ቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።


የማ​ያ​ምኑ አይ​ሁድ ግን ቀኑ​ባ​ቸው፤ ከገ​በ​ያም ክፉ​ዎች ሰዎ​ችን አም​ጥ​ተው፥ ሰዎ​ች​ንም ሰብ​ስ​በው ሀገ​ሪ​ቱን አወ​ኳት፤ ፈለ​ጓ​ቸ​ውም፤ የኢ​ያ​ሶ​ንን ቤትም በረ​በሩ፤ ወደ ሕዝ​ቡም ሊያ​ወ​ጧ​ቸው ሽተው ነበር።


የገ​ለ​ዓ​ድም ሚስት ወን​ዶች ልጆ​ችን ወለ​ደ​ች​ለት፤ ልጆ​ች​ዋም ባደጉ ጊዜ ዮፍ​ታ​ሔን፥ “የሌላ ሴት ልጅ ነህና በአ​ባ​ታ​ችን ቤት አት​ወ​ር​ስም” ብለው አስ​ወ​ጡት።


ከበ​ዓ​ልም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፤ በዚ​ያም አቤ​ሜ​ሌክ ወን​በ​ዴ​ዎ​ች​ንና አስ​ደ​ን​ጋ​ጮ​ችን ቀጠ​ረ​በት፤ እነ​ር​ሱም ተከ​ት​ለ​ውት ሄዱ።


የተ​ጨ​ነ​ቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለ​በት ሁሉ፥ የተ​ከ​ፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​ባ​ሰበ፤ እር​ሱም በላ​ያ​ቸው አለቃ ሆነ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።


ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ስድ​ስቱ መቶ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አን​ኩስ አለፉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos