Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አይ​ሁ​ድም የዚ​ያን ያየ​ውን ሰው ወላ​ጆች እስ​ኪ​ጠሩ ድረስ ዕዉር ሆኖ እንደ ተወ​ለደ፥ እን​ዳ​የም አላ​መ​ኑም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አይሁድ ወደ ወላጆቹ ልከው እስኪያስጠሯቸው ድረስ፣ ሰውየው ዐይነ ስውር እንደ ነበረና እንዳየ አላመኑም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አይሁድ የዚያን ማየት የቻለውን ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ፥ ዐይን ሥውር እንደ ነበረና ማየትም እንደ ጀመረ አላመኑም፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ይህ ሰው ዕውር እንደ ነበረና ዐይኖቹም በኋላ እንዴት እንደ ተከፈቱ ወላጆቹን ጠርተው እስከ ጠየቁአቸው ድረስ የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች አላመኑም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አይሁድ የዚያን ያየውን ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ ዕውር እንደ ነበረ እንዳየም ስለ እርሱ አላመኑም፥

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 9:18
11 Referencias Cruzadas  

እን​ግ​ዲህ እንደ እነ​ዚያ እንደ ካዱት እን​ዳ​ን​ወ​ድቅ፥ ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ገባ ዘንድ እን​ፋ​ጠን።


ወላ​ጆቹ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው ብሎ በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ቢኖር ከም​ኵ​ራብ ይውጣ” ብለው አይ​ሁድ ተስ​ማ​ም​ተው ነበ​ርና።


ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ክብ​ርን የም​ት​መ​ርጡ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን የማ​ትሹ እና​ንተ እን​ዴት ልታ​ምኑ ትች​ላ​ላ​ችሁ?


አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው።


አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴ​ንና ነቢ​ያ​ትን ካል​ሰ​ሙማ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነሣ ቢኖ​ርም እንኳ አይ​ሰ​ሙ​ትም፤ አያ​ም​ኑ​ት​ምም’ አለው።”


ጌታ ሆይ፥ ነገ​ራ​ች​ንን ማን ያም​ነ​ናል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንድ ለማን ተገ​ል​ጦ​አል?


አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።


ሎጥም ወጣ፤ ልጆ​ቹን ለሚ​ያ​ገ​ቡት ለአ​ማ​ቾ​ቹም አላ​ቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ከተማ ያጠ​ፋ​ታ​ልና።” ለአ​ማ​ቾቹ ግን የሚ​ያ​ፌ​ዝ​ባ​ቸው መሰ​ላ​ቸው።


“ዕዉር ሆኖ ተወ​ለደ የም​ት​ሉት ልጃ​ችሁ ይህ ነውን? እን​ግ​ዲያ አሁን እን​ዴት ያያል?” ብለው ጠየ​ቁ​አ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios