Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ሰው በአ​ል​ጋዉ ተኝቶ ባየ ጊዜ በደዌ ብዙ ዘመን እንደ ቈየ ዐውቆ፥ “ልት​ድን ትወ​ዳ​ለ​ህን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ኢየሱስም ይህን ሰው ተኝቶ ባገኘው ጊዜ፣ ለብዙ ጊዜ በዚህ ሁኔታ እንደ ነበር ዐውቆ “ልትድን ትፈልጋለህን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ “ልትድን ትወዳለህን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ኢየሱስ ይህን ሰው እዚያ ተኝቶ አየውና ከብዙ ጊዜ ጀምሮ መታመሙን ዐውቆ፥ “መዳን ትፈልጋለህን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 5:6
9 Referencias Cruzadas  

ጠላት ነፍ​ሴን ከብ​ቦ​አ​ታ​ልና ሕይ​ወ​ቴ​ንም በም​ድር ውስጥ አዋ​ር​ዶ​አ​ታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨ​ለማ አኖ​ሩኝ።


ያል​ፈ​ለ​ጉኝ አገ​ኙኝ፤ ላል​ጠ​የ​ቁ​ኝም ተገ​ኘሁ፤ ስሜን ላል​ጠራ ሕዝብ፥ “እነ​ሆኝ” አል​ሁት።


አስ​ጸ​ያፊ ሥራ​ሽን፥ ምን​ዝ​ር​ና​ሽን፥ ማሽ​ካ​ካ​ት​ሽን፥ የዝ​ሙ​ት​ሽ​ንም መዳ​ራት በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ፥ በሜ​ዳም ላይ አይ​ቻ​ለሁ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ወዮ​ልሽ! ለመ​ን​ጻት እንቢ ብለ​ሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?


ወደ እር​ሱም በደ​ረሰ ጊዜ፥ “ምን ላደ​ር​ግ​ልህ ትወ​ዳ​ለህ?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ እር​ሱም፥ “ጌታ ሆይ፥ ዐይ​ኖች እን​ዲ​ያዩ ነው” አለው።


ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።


በዚ​ያም ከታ​መመ ሠላሳ ስም​ንት ዓመት የሆ​ነው አንድ ሰው ነበር።


ድው​ዩም መልሶ፥ “አዎን ጌታዬ ሆይ፥ ነገር ግን ውኃዉ በተ​ና​ወጠ ጊዜ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ሰው የለ​ኝም፤ እኔ በም​መ​ጣ​በት ጊዜ ሌላው ቀድ​ሞኝ ይወ​ር​ዳል” አለው።


እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።


ሊቀ ካህ​ና​ታ​ችን ለድ​ካ​ማ​ችን መከራ መቀ​በ​ልን የማ​ይ​ችል አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን ከብ​ቻዋ ከኀ​ጢ​አት በቀር እኛን በመ​ሰ​ለ​በት ሁሉ የተ​ፈ​ተነ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos