Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መም​ህ​ራ​ቸው ነህ፤ ነገር ግን እን​ዴት ይህን አታ​ው​ቅም?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ሳለ እነዚህን ነገሮች አታውቅምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው “አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህንን አታውቅምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ይህን አታውቅምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 3:10
28 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።


ሌላ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም አዲስ መን​ፈስ አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ ከሥ​ጋ​ቸ​ውም ውስጥ የድ​ን​ጋ​ዩን ልብ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


ከእ​ነ​ዚያ ወራት በኋላ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጋር የም​ገ​ባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሕጌን በል​ቡ​ና​ቸው አኖ​ራ​ለሁ፤ በል​ባ​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።


ሁሉም ዕው​ራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕው​ቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮ​ኹም ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ማን​ቀ​ላ​ፋ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳሉ።


ይህን ሕዝብ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግኑ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤


አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘ​ወ​ትር ጣል​ኸን? በማ​ሰ​ማ​ሪ​ያህ በጎች ላይስ ቍጣ​ህን ለምን ተቈ​ጣህ?


ጻድ​ቃን አይ​ተው ይፍሩ፤ በእ​ር​ሱም ይሳቁ እን​ዲ​ህም ይበሉ፦


ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም ያደ​ርግ ዘንድ፥ ምስ​ክ​ር​ህ​ንም፥ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ፥ ያዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ለ​ት​ንም ቤት ይሠራ ዘንድ ለልጄ ለሰ​ሎ​ሞን ቅን ልብን ስጠው።”


በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖር፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ እን​ድ​ት​ወ​ድድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም ልብ ያጠ​ራ​ዋል።


እና​ንተ የል​ባ​ች​ሁን ክፋት ግዘሩ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ።


ግዙ​ራ​ንስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ን​ፈስ የም​ና​ገ​ለ​ግ​ለ​ውና የም​ና​መ​ል​ከው እኛ ነን፤ እኛም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​መ​ካ​ለን እንጂ በሥ​ጋ​ችን የም​ን​መካ አይ​ደ​ለም።


በውኑ ለሰው ይም​ሰል አይ​ሁ​ዳዊ መሆን ይገ​ባ​ልን? ለሰው ፊትስ ተብሎ ይገ​ዘ​ሩ​አ​ልን?


የኀ​ጢ​አ​ትን ሰው​ነት ሸለ​ፈት በመ​ግ​ፈፍ በክ​ር​ስ​ቶስ መገ​ረዝ በሰው እጅ የአ​ል​ተ​ደ​ረገ መገ​ረ​ዝን በእ​ርሱ ሆና​ችሁ ተገ​ረ​ዛ​ችሁ።


ከዚ​ህም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤተ መቅ​ደስ በሊ​ቃ​ው​ንት መካ​ከል ተቀ​ምጦ ሲሰ​ማ​ቸ​ውና ሲጠ​ይ​ቃ​ቸው አገ​ኙት።


ከዚ​ህም በኋላ፥ ከዕ​ለ​ታት በአ​ንድ ቀን ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው እን​ዲህ ሆነ፤ ከገ​ሊ​ላና ከይ​ሁዳ መን​ደ​ሮች፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የመጡ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የኦ​ሪት መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እር​ሱም ይፈ​ውስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነበረ።


ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም መልሶ፥ “ይህ ሊሆን እን​ዴት ይቻ​ላል?” አለው።


በሸ​ን​ጎ​ዉም በሕ​ዝቡ ሁሉ ዘንድ የከ​በረ የኦ​ሪት መም​ህር ስሙን ገማ​ል​ያል የሚ​ሉት አንድ ፈሪ​ሳዊ ተነሣ፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ከጉ​ባ​ኤዉ ጥቂት ፈቀቅ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው አዘዘ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios