Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 21:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ኑ፥ ምሳ ብሉ” አላ​ቸው፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አንተ ማነህ? ብሎ ሊጠ​ይ​ቀው የደ​ፈረ የለም፤ ጌታ​ችን እንደ ሆነ ዐው​ቀ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ኢየሱስም “ኑ፤ ቍርስ ብሉ” አላቸው። ጌታ እንደ ሆነ ዐውቀው ስለ ነበር፣ ከደቀ መዛሙርቱ፣ “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ለመጠየቅ የደፈረ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ኢየሱስም “ኑ፤ ብሉ” አላቸው። ከደቀ መዛሙርቱ አንድ እንኳን “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም፤ ጌታ መሆኑን አውቀው ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “ኑ ብሉ” አላቸው። ጌታ ኢየሱስ መሆኑን ሁሉም ዐውቀው ስለ ነበር፥ ከደቀ መዛሙርቱ አንድ እንኳ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ኢየሱስም፦ “ኑ፥ ምሳ ብሉ” አላቸው። ከደቀ መዛሙርቱ አንድ ስንኳ፦ “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊመረምረው የደፈረ አልነበረም፤ ጌታ መሆኑን አውቀው ነበርና።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 21:12
9 Referencias Cruzadas  

አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፤ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።


እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።


እነ​ርሱ ግን ይህን ነገር አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ እን​ዳ​ይ​መ​ረ​ም​ሩት ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነውና፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም እን​ዳ​ይ​ጠ​ይ​ቁት ይፈ​ሩት ነበ​ርና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊጠ​ይ​ቁት እን​ደ​ሚሹ ዐውቆ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ” ስለ አል​ኋ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ነገር እርስ በር​ሳ​ችሁ ትመ​ራ​መ​ራ​ላ​ች​ሁን?


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ታንኳ ገብቶ መቶ አምሳ ሦስት ታላ​ላቅ ዓሣ​ዎ​ችን መልቶ የነ​በ​ረ​ውን መረብ ወደ ምድር ሳበ፤ ብዛ​ቱም ይህን ያህል ሲሆን መረቡ አል​ተ​ቀ​ደ​ደም።


ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፦ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስን፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ከእ​ነ​ዚህ ይልቅ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “በጎ​ችን ጠብቅ” አለው።


በዚ​ያም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ መጡ፤ ከሴት ጋርም ይነ​ጋ​ገር ነበ​ርና ተደ​ነቁ፤ ነገር ግን፥ “ምን ትሻ​ለህ? ወይስ ከእ​ር​ስዋ ጋር ለምን ትነ​ጋ​ገ​ራ​ለህ?” ያለው የለም።


ይኸ​ውም ለሕ​ዝቡ ሁሉ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን አስ​ቀ​ድሞ ለመ​ረ​ጣ​ቸ​ውና ምስ​ክ​ሮች ለሚ​ሆ​ኑት ብቻ ነው እንጂ፤ የመ​ረ​ጣ​ቸው የተ​ባ​ል​ንም እኛ ነን፤ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ ከተ​ነሣ በኋላ ከእ​ርሱ ጋር የበ​ላን የጠ​ጣ​ንም እኛ ነን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos