Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 20:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በዚህ መጽ​ሐፍ ያል​ተ​ጻፈ ብዙ ሌላ ተአ​ም​ራት በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ፊት አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ሌሎች አያሌ ታምራዊ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ሌላ ብዙ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ብዙ ተአምር በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 20:30
10 Referencias Cruzadas  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ የሠ​ራ​ቸው ሌሎች ብዙ ሥራ​ዎች አሉ፤ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ቢጻፍ ግን የተ​ጻ​ፉ​ትን መጻ​ሕ​ፍት ዓለም ስን​ኳን ባል​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበር። ከዐ​ሥራ ሁለቱ ሐዋ​ር​ያት አንዱ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጅ ሐዋ​ር​ያው ዮሐ​ንስ ጌታ​ችን በሥጋ ወደ ሰማይ ባረገ በሠ​ላሳ ዓመት፥ ቄሳር ኔሮን በነ​ገሠ በሰ​ባት ዓመት በዮ​ና​ና​ው​ያን ቋንቋ ለኤ​ፌ​ሶን ሰዎች የጻ​ፈ​ፍው ወን​ጌል ተፈ​ጸመ። ምስ​ጋና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን። አሜን።


የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።


እነ​ር​ሱን ያገ​ኛ​ቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለም​ን​ነ​ሣው ለእኛ ትም​ህ​ር​ትና ምክር ሊሆ​ነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ።


የተ​ጻ​ፈው ሁሉ በመ​ታ​ገ​ሣ​ች​ንና መጻ​ሕ​ፍ​ትን በመ​ታ​መ​ና​ችን ተስ​ፋ​ች​ንን እና​ገኝ ዘንድ እና ልን​ማ​ር​በት ተጻፈ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


በበ​ሽ​ተ​ኞ​ችም ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት ስለ አዩ ብዙ ሰዎች ተከ​ተ​ሉት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios