Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 20:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ይህ​ንም ብሎ እፍ አለ​ባ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​በሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይህን ካለ በኋላም፣ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ይህን ብሎ እፍ አለባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፦ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 20:22
17 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፈጠ​ረኝ፥ ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ እስ​ት​ን​ፋስ ያስ​ተ​ም​ረ​ኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ከም​ድር አፈር ፈጠ​ረው፤ በፊ​ቱም የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋ​ስን እፍ አለ​በት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።


“ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በውኑ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አል​ተ​ቀ​በ​ል​ንም መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዳለ ስንኳ አል​ሰ​ማ​ንም” አሉት።


ወር​ደ​ውም መን​ፈስ ቅዱ​ስን እን​ዲ​ቀ​በሉ ጸለ​ዩ​ላ​ቸው።


ጴጥ​ሮ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ንስሓ ግቡ፤ ሁላ​ች​ሁም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተጠ​መቁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ች​ኋል፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ጸጋ ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋስ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋ​ስም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ! ከአ​ራቱ ነፋ​ሳት ዘንድ ና፤ እነ​ዚህ ሙታን በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በል​ባ​ቸው በል” አለኝ።


ይህ ችግ​ረኛ ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፥ ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው።


ሁሉም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተሞሉ፤ ይና​ገሩ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እንደ አደ​ላ​ቸው መጠ​ንም እየ​ራ​ሳ​ቸው በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ይና​ገሩ ጀመሩ።


ይህ​ንም የሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሰዎች ይቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ አላ​ቸው ስለ መን​ፈስ ቅዱስ ተና​ገረ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ገና ስላ​ል​ከ​በረ መን​ፈስ ቅዱስ ገና አል​ወ​ረ​ደም ነበ​ርና።


በእ​ና​ንተ ዘንድ ይህን ብቻ ላውቅ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን የተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ነውን? ወይስ ሃይ​ማ​ኖ​ትን በመ​ስ​ማት?


ያን​ጊ​ዜም በጴ​ጥ​ሮስ መን​ፈስ ቅዱስ ሞላ​በ​ትና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የሕ​ዝብ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሆይ፥ ስሙ፤


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እንደ እኛ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ከተ​ቀ​በሉ በኋላ እን​ግ​ዲህ በውኃ እን​ዳ​ይ​ጠ​መቁ ውኃን ሊከ​ለ​ክ​ላ​ቸው የሚ​ችል ማነው?” አለ።


“እኔ ከአብ ዘንድ የም​ል​ክ​ላ​ችሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ እር​ሱም ከአብ የሚ​ወጣ የእ​ው​ነት መን​ፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመ​ሰ​ክ​ራል።


እኔም አብን እለ​ም​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከእ​ና​ንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽ​ናኝ ይል​ክ​ላ​ች​ኋል።


“እኔ በእ​ው​ነት የሚ​ሆ​ነ​ውን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ ካል​ሄ​ድሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ ወደ እና​ንተ አይ​መ​ጣ​ምና፤ እኔ ከሄ​ድሁ ግን እር​ሱን እል​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዳግ​መኛ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ አብ እኔን እንደ ላከኝ እን​ዲሁ እኔ እና​ን​ተን እል​ካ​ች​ኋ​ለሁ።”


ኀጢ​ኣ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ያላ​ች​ሁ​ላ​ቸው ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይቅር ያላ​ላ​ች​ኋ​ቸው ግን አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ውም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios