Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የም​ሠ​ራ​ውን አንተ ዛሬ አታ​ው​ቅም፤ ኋላ ግን ታስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ለህ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ኢየሱስም መልሶ፣ “የማደርገውን አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ኢየሱስም መልሶ “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ኢየሱስም “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ኢየሱስም መልሶ፦ “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 13:7
11 Referencias Cruzadas  

እና​ን​ተም፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት፤ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች በም​ት​ሉ​አት ምድር እር​ሻን እንደ ገና ይገ​ዛሉ።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አስ​ቀ​ድ​መው ይህን ነገር አላ​ወ​ቁም፤ ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከከ​በረ በኋላ በዚያ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ፥ ይህ​ንም እንደ አደ​ረ​ጉ​ለት ትዝ አላ​ቸው።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ወደ​ም​ሄ​ድ​በት አሁን ልት​ከ​ተ​ለኝ አት​ች​ልም፤ ኋላ ግን ትከ​ተ​ለ​ኛ​ለህ” አለው።


ወደ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ደረሰ፤ እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ አንተ እግ​ሬን ታጥ​በ​ኛ​ለ​ህን?” አለው።


ነገር ግን አብ በስሜ የሚ​ል​ከው የእ​ው​ነት መን​ፈስ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ እርሱ ሁሉን ያስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋል፤ እኔ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ያሳ​ስ​ባ​ች​ኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos