Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ለነ​ዳ​ያን ይሰጥ ዘንድ ይህን ሽቱ ለሦ​ስት መቶ ዲናር ለምን አል​ሸ​ጡ​ትም?”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ይህ ሽቱ በሦስት መቶ ዲናር ተሸጦ ገንዘቡ ለድኾች ለምን አልተሰጠም?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ይህ ሽቶ ለሦስት መቶ ዲናር ተሽጦ ለድሆች ለምን አልተሰጠም?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ይህ ሽቶ በሦስት መቶ ዲናር ተሸጦ ገንዘቡ ለድኾች ለምን አልተሰጠም?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 “ይህ ሽቱ ለሦስት መቶ ዲናር ተሽጦ ለድሆች ያልተሰጠ ስለ ምን ነው?” አለ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 12:5
16 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡ​ንም ሲያ​ቃ​ል​ሉት ማየት አይ​ገ​ባ​ን​ምና ስለ​ዚህ ልከን ለን​ጉሡ አስ​ታ​ው​ቀ​ናል፤


እርሱ ግን፥ “እና​ንተ አር​ፋ​ች​ኋል፤ ቦዝ​ና​ች​ኋል፤ ስለ​ዚ​ህም፦ ‘እን​ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ሠዋ’ ትላ​ላ​ችሁ።


ቀድሞ ያደ​ር​ጉት የነ​በ​ረ​ውን የጡብ ቍጥር እን​ዲሁ በየ​ቀኑ በእ​ነ​ርሱ ላይ አድ​ር​ጉት፤ ምንም ከእ​ርሱ አታ​ጕ​ድሉ፤ ሥራ ሰል​ች​ተ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ፦ ‘ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እን​ድ​ን​ሠዋ እን​ሂድ’ እያሉ ይጮ​ሃሉ።


“እህ​ልን እን​ሸጥ ዘንድ መባ​ቻው መቼ ያል​ፋል? የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ው​ንም እያ​ሳ​ነ​ስን፥ ሰቅ​ሉ​ንም እያ​በ​ዛን፥ በሐ​ሰ​ተ​ኛም ሚዛን እያ​ታ​ለ​ልን፥


ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና ‘ዕዳህን ክፈለኝ’ ብሎ ያዘና አነቀው።


ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።


ሀብ​ታ​ች​ሁን ሸጣ​ችሁ ምጽ​ዋት ስጡ፤ ሌባ በማ​ያ​ገ​ኝ​በት ነቀ​ዝም በማ​ያ​በ​ላ​ሽ​በት፥ የማ​ያ​ረጅ ከረ​ጢት፥ የማ​ያ​ል​ቅም መዝ​ገብ በሰ​ማ​ያት ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ሰምቶ እን​ዲህ አለው፥ “አን​ዲት ቀር​ታ​ሃ​ለች፤ ሂድና ያለ​ህን ሁሉ ሸጠህ ለነ​ዳ​ያን ስጥ፤ በሰ​ማ​ይም መዝ​ገብ ታገ​ኛ​ለህ፤ መጥ​ተ​ህም ተከ​ተ​ለኝ።”


በወ​ን​ድ​ምህ ዐይን ውስጥ ያለ​ውን ጕድፍ ለምን ታያ​ለህ? በዐ​ይ​ንህ ውስጥ ያለ​ውን ምሰሶ አታ​ይ​ምን?


ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ የነ​በረ ያሲ​ዘው ዘንድ ያለው የስ​ም​ዖን ልጅ አስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ግን እን​ዲህ አለ።


ይህ​ንም ያለ፥ ድሆች አሳ​ዝ​ነ​ውት አይ​ደ​ለም፤ ሌባ ነበ​ርና፥ ሙዳየ ምጽ​ዋ​ቱ​ንም ሲጠ​ብቅ በው​ስጡ ከሚ​ገ​ባው ይወ​ስድ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ነው እንጂ።


ሙዳየ ምጽ​ዋቱ በይ​ሁዳ ዘንድ ነበ​ረና፥ ለበ​ዓል የም​ን​ሻ​ውን ወይም ለነ​ዳ​ያን የም​ን​ሰ​ጠ​ውን ግዛ ያለው የመ​ሰ​ላ​ቸው ነበሩ።


ፊል​ጶ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጥቂት ጥቂት ይወ​ስዱ ዘንድ የሁ​ለት መቶ ዲናር እን​ጀራ አይ​በ​ቃ​ቸ​ውም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos