Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ አት​ፍሪ፤ እነሆ፥ ንጉ​ሥሽ በአ​ህያ ውር​ንጫ ተቀ​ምጦ ይመ​ጣል” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አትፍሪ፤ እነሆ፤ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ይመጣል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “አንቺ የጽዮን ልጅ አትፍሪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል፤” ተብሎ እንደ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “አንቺ የጽዮን ከተማ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ አትፍሪ! እነሆ! ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ተብሎ የተጻፈው ትንቢት እንዲፈጸም ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 12:15
17 Referencias Cruzadas  

ከዚ​ህም በኋላ አቤ​ሴ​ሎም ሰረ​ገ​ላና ፈረ​ሶች፥ በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎች አዘ​ጋጀ።


ንጉ​ሡም ሲባን፥ “ይህ ለአ​ንተ ምን​ድን ነው?” አለው። ሲባም፥ “አህ​ዮቹ የን​ጉሥ ቤተ ሰቦች ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው ዘንድ፥ እን​ጀ​ራ​ውና ተም​ሩም ብላ​ቴ​ኖቹ ይበ​ሉት ዘንድ፥ የወ​ይን ጠጁም በበ​ረሃ የሚ​ደ​ክ​ሙት ይጠ​ጡት ዘንድ ነው” አለ።


ወደ ንጉ​ሡም ገቡ። ንጉ​ሡም አላ​ቸው፥ “የጌ​ታ​ች​ሁን አገ​ል​ጋ​ዮች ይዛ​ችሁ ሂዱ፥ ልጄ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን በበ​ቅ​ሎዬ ላይ አስ​ቀ​ም​ጡት፥ ወደ ግዮ​ንም አው​ር​ዱት፤


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቍ​ጥር ጥቂት የነ​በ​ርህ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እኔ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የሚ​ቤ​ዥ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው።


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ምድር ዳርቻ አዋጅ እን​ዲህ ብሎ ነግ​ሮ​አል፥ “ለጽ​ዮን ልጅ፦ እነሆ፥ መድ​ኀ​ኒ​ትሽ ይመ​ጣል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእ​ርሱ ጋር ሥራ​ውም በፊቱ አለ በሉ​አት።”


አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የአ​ህያ ውር​ንጫ አግ​ኝቶ በእ​ር​ስዋ ላይ ተቀ​መጠ።


ለእ​ርሱ ፈረ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​በዛ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ግብፅ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚ​ያች መን​ገድ መመ​ለ​ስን አት​ድ​ገም ብሎ​አ​ልና።


አር​ባም ልጆች፥ ሠላ​ሳም የልጅ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በሰ​ባም የአ​ህያ ግል​ገ​ሎች ላይ ይቀ​መጡ ነበር። እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስም​ንት ዓመት ገዛ።


በነ​ጫጭ አህ​ዮች ላይ የም​ት​ጫኑ፥ በፍ​ርድ ወን​በር ላይ​የ​ም​ት​ቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም የም​ት​ሄዱ በቃ​ላ​ችሁ ተና​ገሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos