Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 11:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እር​ስዋ ስታ​ለ​ቅስ፥ ከእ​ር​ስዋ ጋር የመጡ አይ​ሁ​ድም ሲያ​ለ​ቅሱ ባየ ጊዜ በልቡ አዘነ፤ በራ​ሱም ታወከ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ኢየሱስም እርሷ ስታለቅስ፣ ተከትለዋትም የመጡት አይሁድም ሲያለቅሱ ባየ ጊዜ መንፈሱ በሐዘን ታውኮ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ኢየሱስም እርሷ ስታለቅስ ከእርሷም ጋር የመጡት አይሁድ ሲያለቅሱ አይቶ በመንፈሱ አዘነ በራሱም ታወከ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ኢየሱስ እርስዋ ስታለቅስና አብረዋት የመጡትም አይሁድ ሲያለቅሱ ባየ ጊዜ በመንፈሱ እጅግ አዝኖ በመታወክ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ኢየሱስም እርስዋ ስታለቅስ ከእርስዋም ጋር የመጡት አይሁድ ሲያለቅሱ አይቶ በመንፈሱ አዘነ በራሱም ታወከ፤

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 11:33
15 Referencias Cruzadas  

ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ ወደ መቃ​ብ​ሩም ሄደ፤ መቃ​ብ​ሩም ዋሻ ነበር፤ በላ​ዩም ታላቅ ድን​ጋይ ተገ​ጥ​ሞ​በት ነበር።


“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ።


ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፤ ሰውየውንም “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። ዘረጋትም፤ እጁም ዳነች።


ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ።


ሊቀ ካህ​ና​ታ​ችን ለድ​ካ​ማ​ችን መከራ መቀ​በ​ልን የማ​ይ​ችል አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን ከብ​ቻዋ ከኀ​ጢ​አት በቀር እኛን በመ​ሰ​ለ​በት ሁሉ የተ​ፈ​ተነ ነው።


እርሱም መልሶ “የማታምን ትውልድ ሆይ! እስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት፤” አላቸው።


ይህ​ንም ተና​ግሮ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ መሰ​ከረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠ​ኛል።”


ከአ​ይ​ሁ​ድም ስለ ወን​ድ​ማ​ቸው ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አ​ቸው ወደ ማር​ያ​ምና ወደ ማርታ የሄዱ ብዙ​ዎች ነበሩ።


ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አት መጥ​ተው በቤት ከእ​ር​ስዋ ጋር የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም ፈጥና ተነ​ሥታ እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ በዚያ ለወ​ን​ድ​ምዋ ልታ​ለ​ቅስ ወደ መቃ​ብሩ የም​ት​ሄድ መስ​ሎ​አ​ቸው ተከ​ተ​ሉ​አት።


እር​ሱም፥ “የት ቀበ​ራ​ች​ሁት?” አለ፤ እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ፥ መጥ​ተህ እይ” አሉት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ባ​ውን አፈ​ሰሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios