Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 9:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ፀሐ​ይን ያዝ​ዛ​ታል፥ አት​ወ​ጣ​ምም፤ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም ያት​ማል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ፀሓይን ያዝዛታል፤ አትወጣምም፤ ከዋክብትንም በማኅተም ያሽጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ፀሐይን ያዝዛታል፥ አትወጣምም፥ ከዋክብትንም ያትማል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ፀሐይ እንዳትወጣ ሊያደርግ ይችላል፤ ከዋክብትም እንዳያበሩ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ፀሐይን ያዝዛታል፥ አትወጣምም፥ ከዋክብትንም ያትማል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 9:7
13 Referencias Cruzadas  

ሰው ሁሉ ደካ​ማ​ነ​ቱን ያውቅ ዘንድ፥ የሰ​ውን ሁሉ እጅ ያት​ማል።


የሰ​ማ​ይም ከዋ​ክ​ብ​ትና ኦሪ​ዎን፥ የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትም ሁሉ ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም፤ ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ ትጨ​ል​ማ​ለች፤ ጨረ​ቃም በብ​ር​ሃኑ አያ​በ​ራም።


እነሆ ነጐ​ድ​ጓ​ድን የሚ​ያ​ጸና፥ ነፋ​ስ​ንም የፈ​ጠረ፥ የመ​ሢ​ሕን ነገር ለሰው የሚ​ነ​ግር፥ ንጋ​ትን ጭጋግ የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ከፍ​ታ​ዎች ላይ የሚ​ረ​ግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።”


በዚ​ያም ቀን ፀሐይ በቀ​ትር ይገ​ባል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ብር​ሃ​ንም በም​ድር ላይ በቀን ይጨ​ል​ማል።


“ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤


ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እጅ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገ​ባ​ዖን እነ​ር​ሱን ባጠ​ፋ​በት፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በጠ​ፉ​በት ቀን ኢያሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ተነ​ጋ​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “በገ​ባ​ዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢ​ሎ​ንም ሸለቆ ጨረቃ፤”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠፋ ድረስ ፀሐ​ይና ጨረቃ በየ​ቦ​ታ​ቸው ቆሙ። ይህም እነሆ በዚህ መጽ​ሐፍ በጊ​ዜው ተጻፈ። ፀሐ​ይም በሰ​ማይ መካ​ከል ቆመች፤ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል አል​ጠ​ለ​ቀ​ችም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos