Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 46:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ፈጣ​ኑም አያ​መ​ል​ጥም፤ ኀያ​ሉም አይ​ድ​ንም፤ በሰ​ሜን በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ በኩል ደክ​መው ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ፈጣኑ መሸሽ አይችልም፤ ብርቱውም አያመልጥም፤ በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ ተሰናክለው ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፈጣኑ መሸሽ አይችልም ኃያሉም አያመልጥም፤ በሰሜን በኩል ባለው በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ እነርሱ ተሰናክለው ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ነገር ግን ፈጣኖች እንኳ ሸሽተው አያመልጡም፤ ጐበዞችም ራሳቸውን ማዳን አይችሉም፤ ከኤፍራጥስ በስተሰሜን በኩል ተሰናክለው ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ፈጣኑ አያመልጥም ኃያሉም አይድንም፥ በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ በኩል ተሰናክለው ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 46:6
22 Referencias Cruzadas  

በእ​ር​ሱም ዘመን የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ሊጋ​ጠም ወደ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉ​ሡም ኢዮ​ስ​ያስ ከእ​ርሱ ጋር ሊጋ​ጠም ወጣ፤ ፈር​ዖ​ንም በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ በመ​ጊዶ ገደ​ለው።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ለግ​ብፅ ንጉሥ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ወስዶ ነበ​ርና የግ​ብፅ ንጉሥ ከዚያ ወዲህ ከሀ​ገሩ አል​ወ​ጣም።


በቤተ መቅ​ደ​ስህ እጆ​ችን ባነ​ሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮ​ኽ​ሁ​ትን የል​መ​ና​ዬን ቃል ስማ።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል።


ስለ​ዚ​ህም ከእ​ነ​ርሱ ብዙ​ዎች በእ​ርሱ ይሰ​ና​ከ​ላሉ፤ ይወ​ድ​ቁ​ማል፤ ይሰ​በ​ሩ​ማል፤ ይጠ​መ​ዱ​ማል፤ ይያ​ዙ​ማል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ከሰ​ሜን ወገን ክፉ ነገር በም​ድ​ሪቱ በተ​ቀ​መጡ ሁሉ ላይ ይፈ​ስ​ሳል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለ​ዚህ አሳ​ዳ​ጆች ይሰ​ና​ከ​ላሉ፤ አያ​ሸ​ን​ፉም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም የማ​ይ​ረሳ ጕስ​ቍ​ል​ና​ቸ​ውን አላ​ወ​ቁ​ምና ፈጽ​መው አፈሩ።


እነሆ ልኬ የሰ​ሜ​ንን ወገ​ኖች ሁሉ፤ ባሪ​ያ​ዬ​ንም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ችም ምድ​ርና በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ሰዎች ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፈጽ​ሜም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጥ​ፋ​ትና ለፉ​ጨት ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ዕፍ​ረት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ከሰ​ሜን ክፉ ነገ​ር​ንና ጽኑ ጥፋ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና ዓላ​ማ​ች​ሁን አንሡ፤ ወደ ጽዮ​ንም ሽሹ፥ ፍጠኑ፥ አት​ዘ​ግዩ።


ያ ቀን ጠላ​ቶ​ቹን የሚ​በ​ቀ​ል​በት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የበ​ቀል ቀን ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በልቶ ይጠ​ግ​ባል፤ በደ​ማ​ቸ​ውም ይሰ​ክ​ራል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በሰ​ሜን ምድር በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ ነውና።


ጦረ​ኞች በጦ​ረ​ኞች ላይ ተሰ​ና​ክ​ለው ሁለቱ በአ​ን​ድ​ነት ወድ​ቀ​ዋ​ልና አሕ​ዛብ ቃል​ሽን ሰም​ተ​ዋል፤ ልቅ​ሶ​ሽም ምድ​ርን ሞል​ቶ​አ​ታል።”


ብዛ​ታ​ቸ​ውም ደከመ፤ ወደ​ቀም፤ አን​ዱም አንዱ ለጓ​ደ​ኛው፦ ተነሥ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ሰይፍ ፊት ወደ ወገ​ና​ችን ወደ ተወ​ለ​ድ​ን​ባት ምድር እን​መ​ለስ አለው።


አንቺ ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ!፥ ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፤ ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለ​ሽም፤ የሚ​ያ​ነ​ሳ​ሽም የለም፤ በዛ​ፎ​ችሽ ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያሽ ያለ​ው​ንም ሁሉ ትበ​ላ​ለች።”


እና​ንተ የብ​ን​ያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላ​ቅም ጥፋት ከመ​ስዕ ይጐ​በ​ኛ​ልና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ለመ​ሸሽ ጽኑ፤ በቴ​ቁሔ መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ በቤ​ት​ካ​ሪም ላይ ምል​ክ​ትን አንሡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos