Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 44:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ነገር ግን እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እና​ደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ ከአ​ፋ​ችን የወ​ጣ​ውን ቃል ሁሉ በር​ግጥ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ በዚያ ጊዜም እን​ጀ​ራን እን​ጠ​ግብ ነበር፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ልን ነበር፤ ክፉም አና​ይም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እናደርጋለን ያልነውን ሁሉ እናደርጋለን፤ አባቶቻችን፣ ነገሥታታችንና ባለሥልጣኖቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች እንዳደረጉት ሁሉ እኛም ለሰማይዋ ንግሥት እናጥናለን፤ የመጠጥ ቍርባን እናፈስስላታለን። በዚያ ጊዜ የተትረፈረፈ ምግብ ነበረን፤ በመልካም ሁኔታ እንገኝ ነበር እንጂ ምንም ክፉ ነገር አልገጠመንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ነገር ግን እኛና አባቶቻችን ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ እንዳደረግነው፥ ለሰማይ ንግሥት ለማጠን የመጠጥንም ቁርባን ለእርሷ ለማፍሰስ ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን፤ በዚያን ጊዜም እንጀራ እንጠግብ ነበር፥ መልካምም ይሆንልን ክፉም አናይም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እኛ እንፈጽማለን ብለን ያሰብነውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ የሰማይ ንግሥት ተብላ ለምትጠራው አምላካችን ዕጣን እናጥናለን፤ እኛና የቀድሞ አባቶቻችን፥ ንጉሦቻችንና መሪዎቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ስናደርግ በነበረው ዐይነት አሁንም የወይን ጠጅ መባ እናቀርብላታለን። ይህን ሁሉ በምናደርግበት በዚያን ጊዜ ብዙ ሲሳይ ነበረን፤ ባለጸጎችም ስለ ነበርን ምንም ችግር አልነበረብንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ነገር ግን እኛና አባቶቻችን ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞች በኢየሩሳሌም አደባባይ እናደርገው እንደ ነበረ፥ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ የመጠጥንም ቍርባን እናፈስስላት ዘንድ ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን፥ በዚያን ጊዜም እንጀራ እንጠግብ ነበር፥ መልካምም ይሆንልን ክፉም አናይም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 44:17
32 Referencias Cruzadas  

ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እን​ጎቻ እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን እን​ዲ​ያ​ፈ​ስሱ ልጆች እን​ጨት ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ አባ​ቶ​ችም እሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ ሴቶ​ችም ዱቄት ይለ​ው​ሳሉ።


ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ​ህን አል​ጠ​በ​ቁም፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸ​ውን ምስ​ክ​ር​ህ​ንም አል​ሰ​ሙም።


እነ​ርሱ ግን ዐመ​ፁ​ብኝ፤ ይሰ​ሙ​ኝም ዘንድ አል​ወ​ደ​ዱም፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ የግ​ብ​ጽ​ንም ጣዖ​ታት አል​ተ​ወም፤ በዚ​ህም ጊዜ በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል ቍጣ​ዬን እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸው ዘንድ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


በአ​ፍህ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ድህ ተስ​ለ​ሃ​ልና ከከ​ን​ፈ​ርህ የወ​ጣ​ውን ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አሉ​አ​ቸው፥ “በሥ​ጋው ምን​ቸት አጠ​ገብ ተቀ​ም​ጠን እስ​ክ​ን​ጠ​ግብ ድረስ እን​ጀ​ራና ሥጋ በም​ን​በ​ላ​በት ጊዜ በግ​ብፅ ምድር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ምነው በሞ​ትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልት​ገ​ድሉ እኛን ወደ​ዚች ምድረ በዳ አም​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና።”


እነ​ዚ​ህም ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ለጥ​ፋት የሆነ፥ ሆዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ክብ​ራ​ቸ​ውም ውር​ደት የሆ​ነ​ባ​ቸው፥ ምድ​ራ​ዊ​ዉ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ናቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ን​ተና ሚስ​ቶ​ቻ​ችሁ በአ​ፋ​ችሁ፦ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ የተ​ሳ​ል​ነ​ውን ስእ​ለ​ታ​ች​ንን በር​ግጥ እን​ፈ​ጽ​ማ​ለን አላ​ችሁ፤ በእ​ጃ​ች​ሁም አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት፤ እን​ግ​ዲህ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁን አጽኑ፤ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈጽሙ።


“እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁም የም​ድ​ርም ሕዝብ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያጠ​ና​ች​ሁ​ትን ዕጣን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በው፥ በል​ቡም ያኖ​ረው አይ​ደ​ለ​ምን?


የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤቶ​ችና የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረ​ከሱ ይሆ​ናሉ፤ እነ​ዚ​ያም በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ ያጠ​ኑ​ባ​ቸው፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸው ቤቶች ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።”


የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ ተዉ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም የሁ​ለ​ቱን እን​ቦ​ሶች ምስ​ሎች አደ​ረጉ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ተከሉ፤ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ሰገዱ፤ በዓ​ል​ንም አመ​ለኩ።


እር​ስ​ዋም፥ “አባቴ ሆይ፥ አፍ​ህን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ፈ​ትህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶ​ችህ በአ​ሞን ልጆች ላይ ተበ​ቅ​ሎ​ል​ሃ​ልና በአ​ፍህ እንደ ተና​ገ​ርህ አድ​ር​ግ​ብኝ” አለ​ችው።


ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ስእ​ለ​ቷን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስለ ስእ​ለቷ ወይም ራስ​ዋን ስላ​ሰ​ረ​ች​በት መሐላ ከአ​ፍዋ የወ​ጣው ነገር አይ​ጸ​ናም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሏ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያነ​ጻ​ታል።


ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።


ንጉሡም እጅግ አዝኖ ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ስለ ተቀመጡት ሊነሣት አልወደደም።


በውኑ በይ​ሁዳ ምድ​ርና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያደ​ረ​ጉ​ትን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ክፋት፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ነገ​ሥ​ታት ክፋት፥ የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ክፋት የሚ​ስ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ክፋት ረስ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልን?።


ስለ​ዚህ፥ አንተ፥ “ጣዖቴ ይህን አድ​ር​ጎ​አል፤ የተ​ቀ​ረ​ጸው ምስ​ሌና ቀልጦ የተ​ሠ​ራው ምስ​ሌም ይህን አዘ​ዙኝ” እን​ዳ​ትል፥ የሚ​ሆ​ነ​ውን ከመ​ሆኑ በፊት ነገ​ር​ሁህ፤ አስ​ረ​ዳ​ሁ​ህም፤


በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው፤


የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ኝም እኔ ብና​ወጥ ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥


በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም።


ሰው ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ቢሳል፥ ወይም መሐ​ላን ቢምል፤ ራሱ​ንም ቢለይ፥ ቃሉን አያ​ር​ክስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድ​ርግ።


ንጉ​ሡም፥ “የመ​ቱ​ኝን የደ​ማ​ስ​ቆን አማ​ል​ክት እፈ​ል​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሶ​ር​ያን ንጉሥ እር​ሱን ረድ​ተ​ው​ታ​ልና እኔ​ንም ይረ​ዱኝ ዘንድ እሠ​ዋ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለ። ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዕን​ቅ​ፋት ሆኑ።


ስለ ክፋ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተዉ፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት ስለ ሠዉ፥ ለእ​ጃ​ቸ​ውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍር​ዴን በእ​ነ​ርሱ ላይ እና​ገ​ራ​ለሁ።


በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ ሄደው ወደ​ሚ​ያ​ጥ​ኑ​ላ​ቸው፥ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ከቶ ወደ​ማ​ያ​ድ​ኗ​ቸው አማ​ል​ክት ይጮ​ኻሉ።


ሕዝቤ ግን ረስ​ተ​ው​ኛል፤ ለከ​ንቱ ነገ​ርም አጥ​ነ​ዋል፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማ​ማ​ውና ወደ ሰን​ከ​ል​ካ​ላው መን​ገድ ለመ​ሄድ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ተሰ​ና​ከሉ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።


ለእ​ና​ን​ተም፦ እንደ አሕ​ዛ​ብና እንደ ምድር ወገ​ኖች እን​ሆ​ና​ለን፤ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ይም እና​መ​ል​ካ​ለን የሚል ከል​ባ​ችሁ የወጣ ዐሳብ አይ​ፈ​ጸ​ም​ላ​ች​ሁም።


በክ​ብር አልጋ ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ በፊት ለፊ​ታ​ቸ​ውም ማዕድ ተዘ​ጋ​ጅታ ነበር፤ በዕ​ጣ​ኔና በዘ​ይ​ቴም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


እድል ፈንታው በእነርሱ ሰብታለችና፥ መብሉም በዝቶአልና ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፥ ለአሽክላውም ያጥናል።


እነ​ር​ሱስ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ውስ​ጥና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አታ​ይ​ምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios