Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 34:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ቃል ኪዳ​ኔን የተ​ላ​ለ​ፉ​ትን ሰዎች፥ በፊቴ ያደ​ረ​ጉ​ትን ቃል ኪዳን ያል​ፈ​ጸ​ሙ​ትን፥ እን​ቦ​ሳ​ው​ንም ቈር​ጠው በቍ​ራጩ መካ​ከል ያለ​ፉ​ትን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኪዳኔን ያፈረሱትንና በፊቴ የገቡትን የኪዳኑን ቃል ያልፈጸሙትን ሰዎች ሥጋውን ሁለት ቦታ ከፍለው በመካከሉ እንዳለፉት፣ እንደ እንቦሳው አደርጋቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ቃል ኪዳኔንም የተላለፉትን ሰዎች፥ እንቦሳውንም ቈርጠው በቁራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳኑን ሕግጋት ያልፈጸሙትን፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ባሪያዎቻችሁን ነጻ ለማውጣት በፊቴ ቃል ኪዳን በገባችሁ ጊዜ አንድን ጥጃ በመቊረጥ ለሁለት ከፍላችሁ በመካከሉ አልፋችኋል፤ ነገር ግን እናንተ ያን ቃል ኪዳንና እኔም ከእስራኤል ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችኋል፤ ስለዚህ እናንተ በጥጃው ላይ እንዳደረጋችሁት እኔ በእናንተ ላይ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ቃል ኪዳኔንም የተላለፉትን ሰዎች፥ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳንን ቃል ያልፈጸሙትን፥

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 34:18
10 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ሁም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወሰ​ደ​ለት፤ በየ​ሁ​ለ​ትም ከፈ​ላ​ቸው፤ የተ​ከ​ፈ​ሉ​ት​ንም በየ​ወ​ገኑ ትይዩ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አል​ቈ​ረ​ጣ​ቸ​ውም።


“አቤቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እን​ደ​ም​ወ​ር​ሳት በምን አው​ቃ​ለሁ?” አለው።


አቤቱ፥ እንደ ቸር​ነ​ትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ኀጢ​አ​ቴን ደም​ስስ።


እነ​ርሱ ግን ቃል ኪዳ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ርስ ሰው ሆኑ፤ በዚ​ያም ላይ ከዱኝ።


በብ​ብ​ታ​ቸው እንደ መሬት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት እንደ ንስር ይመ​ጣል። ቃል ኪዳ​ኔን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ በሕ​ጌም ላይ ዐም​ፀ​ዋ​ልና።


ለሚ​ክ​ዱና እው​ነ​ትን ለሚ​ለ​ውጡ፥ ዐመ​ፅ​ንም ለሚ​ወ​ድዱ ሰዎች ዋጋ​ቸው ቍጣና መቅ​ሠ​ፍት ነው።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ሀገ​ሮች በአ​ን​ዲ​ትዋ ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳ​ኑን በማ​ፍ​ረስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ፥


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል ኪዳን ብታ​ፈ​ርሱ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ በዚያ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፥ ከሰ​ጣ​ች​ሁም ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር ፈጥ​ና​ችሁ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


ሕዝቡ በድ​ለ​ዋል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሰ​ዋል፤ እርም ከሆ​ነ​ውም ነገር ሰር​ቀው ወሰዱ፤ በዕ​ቃ​ቸ​ውም ውስጥ ሸሸ​ጉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos