Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 25:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ለእ​ና​ንተ ጕዳት እን​ዲ​ሆን በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ነገር ግን አልሰማችሁኝም” ይላል እግዚአብሔር፤ “እጃችሁ በሠራው ነገር አስቈጣችሁኝ፤ በራሳችሁም ላይ ክፉ ነገር አመጣችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ለእናንተ ጉዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ አስቆጣችሁኝ እንጂ አልሰማችሁኝም፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እኔን አልሰማችሁኝም፥ እጃችሁ በሠራው ጣዖት አስቆጣችሁኝ።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለእናንተ ጕዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ ታስቈጡኝ ዘንድ አልሰማችሁኝም፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 25:7
15 Referencias Cruzadas  

ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ሥዉ​አ​ቸው፤ ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም ሆኑ፤ ያስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር ለማ​ድ​ረግ ራሳ​ቸ​ውን ሸጡ።


አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ከግ​ብፅ ከአ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊቴ ክፉ ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ አስ​ቈ​ጥ​ተ​ው​ኝ​ማ​ልና።”


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ል​ሱ​አ​ቸው ዘንድ ነቢ​ያ​ትን ይሰ​ድ​ድ​ላ​ቸው ነበር፤ መሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ደ​መ​ጡም።


“ነገር ግን ተመ​ል​ሰው ዐመ​ፁ​ብህ፤ ሕግ​ህ​ንም ወደ ኋላ​ቸው ጣሉት፤ ወደ አን​ተም ይመ​ለሱ ዘንድ የመ​ሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውን ነቢ​ያ​ት​ህን ገደሉ፤ እጅ​ግም አስ​ቈ​ጡህ።


በእኔ ላይ በደልን የሚፈጽሙ ራሳቸውን ይበድላሉ፤ የሚጠሉኝም ሞትን ይወድዳሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ቃሌን እን​ዳ​ይ​ሰሙ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አደ​ን​ድ​ነ​ዋ​ልና እነሆ በዚች ከተ​ማና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ባ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ለሁ።”


በጐ​ሰ​ቈ​ልሽ ጊዜ ተና​ገ​ር​ሁሽ፤ አን​ቺም፦ አል​ሰ​ማም አልሽ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀምሮ ቃሌን አለ​መ​ስ​ማ​ትሽ መን​ገ​ድሽ ነው።


ስለ​ዚህ ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና፤


ይህም የሆ​ነው ቃሌን ስላ​ል​ሰሙ ነው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በማ​ለዳ ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ወደ እነ​ርሱ ሰድ​ጃ​ለ​ሁና፤ እና​ንተ ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከይ​ሁዳ ወገን መካ​ከል ቅሬታ እን​ዳ​ይ​ቀ​ር​ላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ንና ሴትን፥ ብላ​ቴ​ና​ንና የሚ​ጠባ ሕፃ​ንን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራ​ሳ​ችሁ ላይ ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ታጠፉ ዘንድ፥ በም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መረ​ገ​ሚ​ያና መሰ​ደ​ቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመ​ቀ​መጥ በገ​ባ​ች​ሁ​ባት በግ​ብፅ ምድር ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት በማ​ጠ​ና​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ለምን ታስ​ቈ​ጡ​ኛ​ላ​ችሁ?


የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፣ እነርሱ ግን አልሰሙም፥ እኔንም አላደመጡም፣ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል እግዚአብሔር።


አም​ላክ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ኑኝ፤ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አስ​ቈ​ጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝ​ብም አስ​ቈ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos