Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 15:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! የሚ​ራ​ራ​ልሽ ማን ነው? የሚ​ያ​ዝ​ን​ል​ሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅ​ን​ነ​ትሽ ይጠ​ይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ኢየሩሳሌም ሆይ፤ የሚራራልሽ ማን ነው? ማንስ ያለቅስልሻል? ደኅንነትሽንስ ማን ጐራ ብሎ ይጠይቃል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ኢየሩሳሌም ሆይ! የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ቆም ብሎ የሚጠይቅ ማነ ነው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ማን ይራራላችኋል? የሚያዝንላችሁስ ማን ነው? ለአንድ አፍታ ቆም ብሎ ስለ ሁኔታችሁስ የሚጠይቅ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማነ ነው?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 15:5
15 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ ወዳ​ጆቼ ሆይ፤ ማሩኝ፤ ማሩኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ዳስ​ሳ​ኛ​ለ​ችና።


ሙሴም አማ​ቱን ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እጅ ነሣው፤ ሳመ​ውም፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ሰላ​ምታ ተሰ​ጣጡ፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ገቡ።


አሁ​ንም እነ​ዚህ ሁለቱ ይጠ​ብ​ቁ​ሻል፤ ማን ያስ​ተ​ዛ​ዝ​ን​ሻል? እነ​ር​ሱም ጥፋ​ትና ውድ​ቀት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እን​ግ​ዲህ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናሽ ማን ነው?


ሰው​ንና ወን​ድ​ሙን፥ አባ​ቶ​ች​ንና ልጆ​ችን በአ​ንድ ላይ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አላ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ም​ራ​ቸ​ው​ምም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላ​ሜን፥ ቸር​ነ​ቴ​ንና ምሕ​ረ​ቴን፥ ከዚህ ሕዝብ አስ​ወ​ግ​ጄ​አ​ለ​ሁና ልቅሶ ወዳ​ለ​በት ቤት አት​ግባ፤ ታለ​ቅ​ስና ታዝ​ንም ዘንድ አት​ሂድ።


ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”


ፌ። ጽዮን እጅ​ዋን ዘረ​ጋች፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ትም የለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በያ​ዕ​ቆብ ዙሪያ ያሉ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁት አዘዘ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ረከ​ሰች ሆና​ለች።


የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ባድማ ሆናለች፣ የሚያለቅስላትስ ማን ነው? የሚያጽናናትንስ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል።


ከመ​ን​ገ​ዱም ፈቀቅ ብለው ወደ ጐል​ማ​ሳው ሌዋዊ ቤት ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላ​ም​ታም ሰጡት።


ሰላ​ም​ታም ይሰ​ጡ​ሃል፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ሁለት ዳቦ​ዎ​ችም ይሰ​ጡ​ሃል፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም ትቀ​በ​ላ​ለህ።


ዳዊ​ትም ዕቃ​ውን በዕቃ ጠባ​ቂው እጅ አኖ​ረው፤ ወደ​ሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ሮጦ ሄደ፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠየቀ።


ዳዊ​ትም ዐሥር ብላ​ቴ​ኖ​ችን ላከ፤ ለብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አለ፥ “ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወጥ​ታ​ችሁ ወደ ናባል ሂዱ፤ በስ​ሜም ሰላም በሉት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos