Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 41:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አና​ጢ​ውም አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን፥ በመ​ዶ​ሻም የሚ​ያ​ሳ​ሳ​ውን መስፍ መች​ውን አጽ​ናና፤ ስለ ማጣ​በቅ ሥራ​ውም፥ “መል​ካም ነው” አለ፤ እን​ዳ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ስም በች​ን​ካር አጋ​ጠ​መው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የእጅ ጥበብ ባለሙያው የወርቅ አንጥረኛውን ያበረታታዋል፤ በመዶሻ የሚያሳሳውም፣ በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያነቃቃዋል፤ ስለ ብየዳም ሥራው፣ “መልካም ነው” ይለዋል፤ የጣዖቱ ምስል እንዳይወድቅም በምስማር ያጣብቀዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አናጢውም አንጥረኛውን፥ በመዶሻም የሚያሳሳውን በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያጽናናዋል፥ ስለ ብየዳ ሥራውም፦ “መልካም ነው” ይለዋል፤ እንዳይላቀቅም በችንካር ያጋጥመዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የእጅ ጥበብ ዐዋቂው ወርቅ አንጥረኛን ያበረታታዋል፤ ጣዖት ጠርቦ በመዶሻ የሚያለሰልሰውም በመስፍ ላይ የሚመታውን ‘አይዞህ በርታ! ብየዳው መልካም ነው!’ ይለዋል። እንዳይንቀሳቀስም ጣዖቱን በምስማር ይቸነክሩታል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አናጢውም አንጥረኛውን፥ በመዶሻም የሚያሳሳውን መስፍ መችውን አጽናና፥ ስለ ማጣበቅ ሥራውም፦ መልካም ነው አለ፥ እንዳይንቀሳቀስም በችንካር አጋጠመው።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 41:7
9 Referencias Cruzadas  

ሁሉም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ይከ​ራ​ከ​ራል፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ወን​ድሙ ይረ​ዳው ነበር፤ ወን​ድ​ሙ​ንም፦ አይ​ዞህ ይለው ነበር።


የሠ​ራ​ተ​ኛና የአ​ን​ጥ​ረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተ​ር​ሴስ ጥፍ​ጥፍ ብር፥ ከአ​ፌ​ዝም ወርቅ ይመ​ጣል፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም ሰማ​ያ​ዊና ቀይ ግምጃ ነው፤ ሁሉም የብ​ል​ሃ​ተ​ኞች ሥራ ናቸው።


እር​ሱም፥ “የሠ​ራ​ኋ​ቸ​ውን አማ​ል​ክ​ቴን፥ ካህ​ኑ​ንም ይዛ​ችሁ ሄዳ​ች​ኋል፤ ለእኔ ምን ተዋ​ች​ሁ​ልኝ? እና​ን​ተስ፦ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ እን​ዴት ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos