Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 41:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ከአ​ሕ​ዛ​ብና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው የሚ​ና​ገር የለ​ምና፥ ከየ​ትም እንደ ሆኑ ብጠ​ይ​ቃ​ቸው አይ​መ​ል​ሱ​ል​ኝም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ተመለከትሁ ማንም አልነበረም፤ ከመካከላቸው አማካሪ የለም፤ ስጠይቅም መልስ የሚሰጥ የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ብመለከት ማንም አልነበረም፤ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ዞር ብዬ በተመለከትኩ ጊዜ ማንም አልነበረም፤ ከአማልክትም መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም፤ ጥያቄም ስጠይቅ ማንም መልስ የሚሰጥ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ብመለከት ማንም አልነበረም፥ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 41:28
9 Referencias Cruzadas  

በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።


እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አል​ነ​በ​ረም፤ ተጣ​ራሁ፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ እጄ ለማ​ዳን ጠን​ካራ አይ​ደ​ለ​ምን? ወይስ ለማ​ዳን አል​ች​ል​ምን? እነሆ፥ በገ​ሠ​ጽሁ ጊዜ ባሕ​ርን አደ​ር​ቃ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ውኃም በማ​ጣት ዐሣ​ዎ​ቻ​ቸው ይሞ​ታሉ፤ በጥ​ማ​ትም ያል​ቃሉ።


ሰውም እን​ደ​ሌለ አየ፤ የሚ​ረ​ዳም ሰው እን​ደ​ሌለ ተረዳ፤ ሰለ​ዚህ በክ​ንዱ ደገ​ፋ​ቸው፤ በይ​ቅ​ር​ታ​ውም አጸ​ና​ቸው።


የሚ​ረ​ዳም እን​ደ​ሌለ አየሁ፤ የሚ​ያ​ግ​ዝም እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ፤ ስለ​ዚህ በገዛ ክንዴ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬም ወደ​ቀ​ች​ባ​ቸው።


እኔም ለሰ​ይፍ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሁላ​ች​ሁም በሰ​ይፍ ትገ​ደ​ላ​ላ​ችሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገር አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ያል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ት​ንም መረ​ጣ​ችሁ እንጂ በጠ​ራ​ኋ​ችሁ ጊዜ አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ል​ኝ​ምና፥ በተ​ና​ገ​ር​ሁም ጊዜ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝ​ምና።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos