Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 34:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ገ​ደ​ሉት በድ​ና​ቸው ይጣ​ላል፤ የሬ​ሳ​ቸ​ውም ግማት ይሸ​ታል፤ ተራ​ሮ​ቹም ከደ​ማ​ቸው የተ​ነሣ ይር​ሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከእነርሱም የተገደሉት ወደ ውጭ ይጣላሉ፤ ሬሳቸው ይከረፋል፤ ተራሮችም ደም በደም ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ። ሬሳቸውም ይከረፋል፤ ተራሮችም በደማቸው ይርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሬሳቸው የትም ተጥሎ ይበሰብሳል እንጂ አይቀበርም፤ ተራራዎችም በደማቸው ይጥለቀለቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ። የሬሳቸውም ግማት ይሸታል፥ ተራሮችም ከደማቸው የተነሣ ይርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 34:3
20 Referencias Cruzadas  

በሐ​ሣር እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ፥ ክብ​ራ​ች​ሁን ወዴት ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ? በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


ኀያ​ላን ከእ​ነ​ርሱ ጋር፥ ወይ​ፈ​ኖ​ችም ከኮ​ር​ማ​ዎች ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ራ​ቸ​ውም በደም ትሰ​ክ​ራ​ለች፤ በስ​ባ​ቸ​ውም ትወ​ፍ​ራ​ለች።


ወጥ​ተ​ውም በእኔ ያመ​ፁ​ብ​ኝን ሰዎች ሬሳ​ቸ​ውን ያያሉ፤ ትላ​ቸው አይ​ሞ​ትም፤ እሳ​ታ​ቸ​ውም አይ​ጠ​ፋም፤ ለሥጋ ለባ​ሽም ሁሉ ምሳሌ ይሆ​ናሉ።”


አህ​ያም እን​ደ​ሚ​ቀ​በር ይቀ​በ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በር ወደ ውጭ ተጐ​ትቶ፥ በው​ራጅ ጨርቅ ተጠ​ቅ​ልሎ ይጣ​ላል።”


በዚ​ያም ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግዳ​ዮች ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆ​ናሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ በም​ድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ እንጂ አይ​ሰ​በ​ሰ​ቡም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም።


ወይም በዚ​ያች ምድር ላይ ቸነ​ፈ​ርን ብሰ​ድድ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም ከእ​ር​ስዋ አጠፋ ዘንድ መዓ​ቴን በደም ባፈ​ስ​ስ​ባት፥


በሰፊ ምድረ በዳም እጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ የሰ​ማ​ይ​ንም ወፎች ሁሉ አሳ​ር​ፍ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የም​ድ​ር​ንም አራ​ዊት ሁሉ ከአ​ንተ አጠ​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! በደም እንደ በደ​ልህ ደም ያሳ​ድ​ድ​ሃል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በቸ​ነ​ፈ​ርና በደም እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ዶፍም፥ የበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ፥ እሳ​ትና ድኝም በእ​ር​ሱና በጭ​ፍ​ሮቹ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር በአሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘ​ን​ባ​ለሁ።


“በዚ​ያም ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በባ​ሕር ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ል​ፉ​በ​ትን ሸለቆ፥ የመ​ቃ​ብ​ርን ስፍራ ለጎግ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ል​ፉ​ት​ንም ይከ​ለ​ክ​ላል፤ በዚ​ያም ጎግ​ንና ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ይቀ​ብ​ራሉ፤ የሸ​ለ​ቆ​ው​ንም ስም የጎግ መቃ​ብር ብለው ይጠ​ሩ​ታል።


አን​ተና ጭፍ​ሮ​ችህ ሁሉ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉ ሕዝብ በም​ድረ በዳ ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለሚ​ና​ጠቁ ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊ​ትም መብል አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


የሰ​ሜ​ን​ንም ሠራ​ዊት ከእ​ና​ንተ ዘንድ አር​ቃ​ለሁ፤ ወደ በረ​ሃና ወደ ምድረ በዳ እሰ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ፊቱን ወደ መጀ​መ​ሪ​ያው ባሕር፥ ጀር​ባ​ው​ንም ወደ ኋለ​ኛው ባሕር አድ​ርጌ አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ትዕ​ቢ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ግማቱ ይወ​ጣል፤ ክር​ፋ​ቱም ይነ​ሣል።”


“በግ​ብፅ እንደ ሆነው ሞትን ሰደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ይፍ ገደ​ልሁ፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ማ​ረ​ክሁ፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁም እሳ​ትን ሰድጄ አጠ​ፋ​ኋ​ችሁ፤ በዚ​ህም ሁሉ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍም ይንቦገቦጋል፥ ጦርም ይብለጨለጫል፣ የተገደሉትም ይበዛሉ፥ በድኖችም በክምር ይከመራሉ፥ ሬሳቸውም አይቈጠርም፣ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።


የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos