Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 24:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እነሆ፥ ምድር መፈ​ታ​ትን ትፈ​ታ​ለች፤ ፈጽ​ማም ትበ​ረ​በ​ራ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ዲህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ምድር ፈጽሞ ባድማ ትሆናለች፤ ጨርሶም ትበዘበዛለች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሯልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ምድር ፈጽሞ ባድማ ትሆናለች፤ ፈጽማም ትበላሻለች፤ ጌታ ይህን ቃል ተናግሮአል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ምድሪቱ ተበዝብዛ ባዶዋን ትቀራለች፤ ይህ ሁሉ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ስለ ሆነ ይፈጸማል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ምድር መፈታትን ትፈታለች፥ ፈጽማም ትበላሻለች፥ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሮአልና።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 24:3
16 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለ​ምን ያጠ​ፋ​ታል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ጋ​ታል፤ ይገ​ለ​ብ​ጣ​ት​ማል፤ በእ​ር​ስ​ዋም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ይበ​ት​ናል።


እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለኝ፥ “ከተ​ሞች የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አጥ​ተው እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ ቤቶ​ችም ሰው አልቦ እስ​ኪ​ሆኑ፥ ምድ​ርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስ​ክ​ት​ቀር ድረስ ነው፤”


የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍም ተናግሮአልና ሰው እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፥ የሚያስፈራውም የለም።


ስለ​ዚህ፥ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶች፥ ለፈ​ሳ​ሾ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎች፥ ለም​ድረ በዳ​ዎች፥ ባዶ ለሆ​ኑ​ትና ለፈ​ረ​ሱት፥ በዙ​ሪያ ላሉት ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ምር​ኮና መሣ​ለ​ቂያ ለሆ​ኑት ከተ​ሞች እን​ዲህ ይላል፦


በዚያ ቀን፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በታ​መ​ነው ስፍራ የተ​ተ​ከ​ለው ችን​ካር ይወ​ል​ቃል፤ ተሰ​ብ​ሮም ይወ​ድ​ቃል፤ በእ​ር​ሱም ላይ የተ​ሰ​ቀ​ለው ሸክም ይጠ​ፋል፤” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ከቀ​ስ​ተ​ኞች ቍጥር የቀ​ሩት፥ የቄ​ዳር ልጆች ኀያ​ላን፥ ያን​ሳሉ፤” የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲ​ፈ​ጸም፥ ምድ​ሪቱ ሰን​በ​ትን በማ​ድ​ረ​ግዋ እስ​ክ​ታ​ርፍ ድረስ፥ በተ​ፈ​ታ​ች​በ​ትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ሰን​በ​ትን አገ​ኘች።


ዛሬም እን​ዳሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣና በመ​ቅ​ሠ​ፍት፥ በታ​ላ​ቅም መዓት ከም​ድ​ራ​ቸው ነቀ​ላ​ቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላ​ቸው።


ምድ​ርም በሁ​ለ​ን​ተ​ናዋ ዲንና ጨው፥ መቃ​ጠ​ልም እንደ ሆነ​ባት፥ እን​ዳ​ይ​ዘ​ራ​ባ​ትም፥ እን​ዳ​ታ​በ​ቅ​ልም፥ ማና​ቸ​ውም ሣርና ልም​ላ​ሜም እን​ዳ​ይ​ወ​ጣ​ባት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣ​ውና በመ​ዓቱ እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ እንደ አዳ​ማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥


ስሙ፤ አድ​ምጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና አት​ታ​በዩ።


ባድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ገ​ረ​ዝም፤ አይ​ኰ​ተ​ኰ​ትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵር​ን​ች​ትና እሾህ ይበ​ቅ​ል​በ​ታል፤ ዝና​ብ​ንም እን​ዳ​ያ​ዘ​ን​ቡ​በት ደመ​ና​ዎ​ችን አዝ​ዛ​ለሁ።


ሕዝቡ እንደ ካህኑ፥ ባሪ​ያ​ውም እንደ ጌታው ባሪ​ያ​ይ​ቱም እንደ እመ​ቤቷ፥ የሚ​ሸ​ጠ​ውም እን​ደ​ሚ​ገ​ዛው፥ ተበ​ዳ​ሪ​ውም እንደ አበ​ዳ​ሪው፥ ዕዳ ከፋ​ዩም እንደ ዕዳ አስ​ከ​ፋዩ ይሆ​ናል።


ምድ​ርም አለ​ቀ​ሰች፤ ጠፋ​ችም፤ ዓለም ተገ​ለ​በ​ጠች፤ የም​ድ​ርም ታላ​ላ​ቆች አለ​ቀሱ።


በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፥ እነርሱም፦ ፈጽመን ጠፍተናል፥ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፥ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል ይላሉ።


እነሆ፥ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ሕዝቡ የተ​በ​ዘ​በ​ዘና የተ​ዘ​ረፈ ነው፤ ወጥ​መድ በሁ​ሉም ቦታ በዋ​ሻ​ዎ​ችና እነ​ር​ሱን በሸ​ሸ​ጉ​ባ​ቸው ቤቶች ተጠ​ም​ዶ​አል፤ ብዝ​በዛ ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ድ​ንም የለም፤ ምር​ኮም ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ስ​ጥ​ላ​ቸ​ውም የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios