Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 24:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እነ​ር​ሱም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ተዘ​ግ​ቶ​ባ​ቸ​ውም በግ​ዞት ቤት ይኖ​ራሉ፤ ከብዙ ትው​ል​ድም በኋላ ይጐ​በ​ኛሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በጕድጓድ ውስጥ እንዳሉ እስረኞች፣ በአንድ ላይ ይታጐራሉ፤ በእስር ቤት ይዘጋባቸዋል፣ ከብዙ ቀንም በኋላ ለፍርድ ይቀርባሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በጉድጓድ እንደሚከማቹ እስረኞች በአንድነት ይከማቻሉ፤ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፥ ከብዙ ቀንም በኋላ ይቀጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር ነገሥታትን በአንድነት ሰብስቦ በምድር ውስጥ ባለ እስር ቤት ውስጥ እንዳሉ እስረኞች እንዲኖሩ ያደርጋል፤ ከብዙ ቀኖችም በኋላ ይቀጣቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ግዞተኞች በጕድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ፥ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፥ ከብዙ ቀንም በኋላ ይጎበኛሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 24:22
11 Referencias Cruzadas  

ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ።


እነሆ፥ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ሕዝቡ የተ​በ​ዘ​በ​ዘና የተ​ዘ​ረፈ ነው፤ ወጥ​መድ በሁ​ሉም ቦታ በዋ​ሻ​ዎ​ችና እነ​ር​ሱን በሸ​ሸ​ጉ​ባ​ቸው ቤቶች ተጠ​ም​ዶ​አል፤ ብዝ​በዛ ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ድ​ንም የለም፤ ምር​ኮም ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ስ​ጥ​ላ​ቸ​ውም የለም።


ከብዙ ዘመ​ንም በኋላ ትፈ​ለ​ጋ​ለህ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ በነ​በሩ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰ​በ​ሰ​በች፥ ከሰ​ይፍ ወደ ተመ​ለ​ሰች ምድር ትገ​ባ​ለህ፤ እር​ስ​ዋም ከሕ​ዝብ ውስጥ ወጥ​ታ​ለች፤ ሁሉም በሰ​ላም ይቀ​መ​ጡ​በ​ታል።


በም​ድር ላይ በሚ​ኖሩ፥ ፍር​ሀ​ትና ገደል ወጥ​መ​ድም አሉ።


በሐ​ሣር እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ፥ ክብ​ራ​ች​ሁን ወዴት ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ? በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃ​ቃት ውስጥ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።


የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፤


እናንተ በተስፋ የምትኖሩ እስሮች ሆይ፥ ወደ ጽኑ አምባ ተመለሱ፣ ሁለት እጥፍ አድርጌ እንድመልስልሽ ዛሬ እነግርሻለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios