Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 23:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከሰባ ዓመ​ትም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጢሮ​ስን በይ​ቅ​ርታ ይጐ​በ​ኛ​ታል፤ ወደ ጥን​ቷም ትመ​ለ​ሳ​ለች፤ ደግ​ሞም ለዓ​ለም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መና​ገ​ሻና መና​ገጃ ትሆ​ና​ለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሰባው ዓመት ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞው የግልሙትና ሥራዋ ተመልሳ፣ በምድር ላይ ካሉት የዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋራ በንግዷ ትገለሙታለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከሰባ ዓመትም በኋላ ጌታ ጢሮስን ይጎበኛታል፥ ወደ ዋጋዋም ትመለሳለች፥ ደግሞም በምድር ፊት ላይ ከሆኑ ከዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር ትገለሙታለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከሰባ ዓመት በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞ የንግድ ሥራዋ እንድትመለስ ያደርጋታል፤ በምድር ላይ ከሚገኙ መንግሥታት ሁሉ ጋር ታመነዝራለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከሰባ ዓመትም በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጎበኛታል፥ ወደ ዋጋዋም ትመለሳለች፥ ደግሞም በምድር ፊት ላይ ከሆኑ ከዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር ትገለሙታለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 23:17
22 Referencias Cruzadas  

ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፣ እርስዋም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች።


በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤


እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለነውረኛ ረብ የማይስገበገቡ፥


የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥


ስም​ዖ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ አሕ​ዛ​ብን ይቅር እን​ዳ​ላ​ቸ​ውና ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ለስሙ ሕዝ​ብን እንደ መረጠ ተና​ግ​ሮ​አል።


የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ቅሬታ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፣ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳልና በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።


የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፥ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰባቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።


“ስለ​ዚህ እነሆ አንቺ ባደ​ረ​ግ​ሽው ሥራ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በነ​በ​ረው ደም ላይ በእጄ አጨ​በ​ጨ​ብሁ።


በየ​መ​ን​ገዱ ራስ የም​ን​ዝ​ር​ና​ሽን ስፍራ ሠር​ተ​ሻል፤ በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩም ከፍ ያለ​ውን ቦታ​ሽን አድ​ር​ገ​ሻል። ዋጋ​ዋን እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ እንደ ጋለ​ሞ​ታም አል​ሆ​ን​ሽም።


አካ​ላ​ቸ​ውም ከወ​ፈረ ከጐ​ረ​ቤ​ቶ​ችሽ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ልጆች ጋር አመ​ነ​ዘ​ርሽ፤ እኔ​ንም ታስ​ቆጭ ዘንድ ዝሙ​ት​ሽን አበ​ዛሽ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰባው ዓመት በባ​ቢ​ሎን በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ እጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ለሁ፥ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ችሁ ዘንድ መል​ካ​ሚ​ቱን ቃሌን እፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ስለ ተሳ​ል​ኸው ስእ​ለት ሁሉ የአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዪ​ቱን ዋጋና የው​ሻ​ውን ዋጋ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አታ​ቅ​ርብ፤ ሁለ​ቱም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ጢሮስ እንደ አንድ ንጉሥ ዘመን ወይም እንደ አንድ ሰው ዘመን ሰባ ዓመት ያህል የተ​ረ​ሳች ትሆ​ና​ለች፤ ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢ​ሮስ በጋ​ለ​ሞታ ዘፈን እን​ደ​ሚ​ሆን እን​ዲሁ ይሆ​ናል።


አንቺ የተ​ረ​ሳሽ ጋለ​ሞታ ሆይ፥ መሰ​ንቆ ያዢ፤ በከ​ተማ ላይም ዙሪ፤ መታ​ሰ​ቢ​ያም ይሆ​ን​ልሽ ዘንድ ዜማን አሳ​ምሪ፤ ዘፈ​ን​ሽ​ንም አብዢ።


በየ​መ​ን​ገዱ ራስ ከፍ ያለ​ውን ቦታ​ሽን ሠራሽ፤ ውበ​ት​ሽ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ ለመ​ን​ገድ አላ​ፊም ሁሉ እግ​ር​ሽን ገለ​ጥሽ፤ ዝሙ​ት​ሽ​ንም አበ​ዛሽ።


ይህ​ችም ምድር ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ ለእ​ነ​ዚ​ህም አሕ​ዛ​ብና ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገ​ዛሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios