Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ታላቅ ሥራ ሠር​ቶ​አ​ልና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ዘምሩ፤ ይህ​ንም በም​ድር ሁሉ ላይ አስ​ታ​ውቁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቷልና፤ ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለጌታ ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና፤ ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለ ታላቅ ሥራውም ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ይህም ታላቅ ሥራው በዓለም ሁሉ እንዲታወቅ አድርጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ታላቅ ሥራ ሰርቶአልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፥ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 12:5
16 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ አሕ​ዛብ ደነ​ገጡ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ፥ ምድ​ርን አነ​ዋ​ወ​ጣት።


በዚያ ጊዜም ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይህን መዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመሩ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፦ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ም​ራ​ለን፤ በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጣለ።


ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።


ለጽ​ዮን የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ከፍ ወዳ​ለው ተራራ ውጣ፤ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ድም​ፅ​ህን በኀ​ይል አንሣ፤ አት​ፍራ፤ ለይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች፦ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ! ብለህ ንገር።


ማር​ያ​ምም አስ​ቀ​ድማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ምር አለች፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ምር በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጥሎ​አ​ልና።”


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኀይል ማን ይና​ገ​ራል? ምስ​ጋ​ና​ው​ንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደ​ር​ጋል?


እን​ዴት ለጥ​ፋት ሆኑ! በድ​ን​ገት አለቁ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ጠፉ።


እነ​ዚህ ድም​ፃ​ቸ​ውን ያነ​ሣሉ፤ በም​ድር የቀ​ሩ​ትም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ የባ​ሕ​ርም ውኃ ይና​ወ​ጣል።


ወደ ባሕር የም​ት​ወ​ርዱ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ የም​ት​ጓዙ ሁሉ፥ ደሴ​ቶ​ችና በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ መዝ​ሙር ዘምሩ፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ስሙን አክ​ብሩ።


ምድረ በዳ​ውና ከተ​ሞ​ችዋ፥ የቄ​ዳ​ርም ነዋ​ሪ​ዎ​ችና መን​ደ​ሮች ድም​ፃ​ቸ​ውን ያንሡ፤ በዋ​ሻም የሚ​ኖሩ እልል ይበሉ፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ይከ​በ​ራ​ልና የም​ድር መሠ​ረ​ቶች መለ​ከ​ትን ይንፉ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በው​ስ​ጣ​ቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios