Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ያን​ጊዜ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች፥ ዛፎ​ችም ይጠ​ፋሉ። ነፍ​ስና ሥጋ​ንም ይበ​ላል፤ የሚ​ሸ​ሽም ከሚ​ነ​ድድ የእ​ሳት ነበ​ል​ባል እን​ደ​ሚ​ሸሽ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሕመምተኛ እየመነመነ እንደሚሞት፣ የደኑን ክብርና የለማውን ዕርሻ፣ ነፍስና ሥጋንም ፈጽሞ ያጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሕመምተኛ እየመነመነ እንደሚሞት፤ የደኑን ክብርና የለማውን ዕርሻ፤ ነፍስና ሥጋንም ፈጽሞ ያጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ብርቱ ደዌ ሰውን አሰልስሎ እንደሚገድል፥ የተዋቡ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖቹና ለምለም የእርሻ ቦታዎቹ ይደመሰሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከነፍስም እስከ ሥጋ ድረስ የዱሩንና የሚያፈራውን እርሻ ክብር ይበላል፥ ይህም የታመመ ሰው እንደሚሰለስል ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 10:18
10 Referencias Cruzadas  

አን​ተስ በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ እጅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ተገ​ዳ​ደ​ርህ፤ እን​ዲ​ህም አልህ፦ በሰ​ረ​ገ​ላዬ ብዛት ወደ ተራ​ሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባ​ኖስ ጥግ እወ​ጣ​ለሁ፤ ረጃ​ጅ​ሞ​ች​ንም ዝግ​ባ​ዎች የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም ጥዶች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ ወደ ሀገ​ሩም ዳር​ቻና ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ዱር እገ​ባ​ለሁ።


ቍጣ​ህና ትዕ​ቢ​ትህ ወደ ጆሮዬ ደር​ሶ​አ​ልና ስለ​ዚህ ስና​ጋ​ዬን በአ​ፍ​ን​ጫህ፥ ልጓ​ሜ​ንም በከ​ን​ፈ​ርህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ጣ​ህ​በት መን​ገ​ድም እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ብ​ርህ ላይ ውር​ደ​ትን፥ በጌ​ጥህ ላይም የሚ​ነ​ድና የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳ​ትን ይሰ​ድ​ዳል።


በረዶ ቢወ​ርድ አይ​ደ​ር​ስ​ባ​ች​ሁም፤ በዛፍ ሥር የሚ​ኖሩ ሰዎች በበ​ረሃ እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች ታም​ነው ይኖ​ራሉ።


አን​ተም በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ በኩል እን​ዲህ ብለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፦ በሰ​ረ​ገ​ላዬ ብዛት ወደ ተራ​ሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባ​ኖስ ራስ ወጥ​ቻ​ለሁ፤ ረዣ​ዥ​ሞ​ቹ​ንም ዝግ​ባ​ዎች፥ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም ጥዶች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ ወደ ከፍ​ታ​ውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገ​ባ​ለሁ፤


ኀጢ​አት እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል፤ እሳት እንደ በላ​ችው ደረቅ ሣር ይቃ​ጠ​ላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃ​ጠ​ላል፤ በተ​ራ​ራ​ዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃ​ጠ​ላል።


እንደ ሥራ​ች​ሁም ፍሬ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዱ​ር​ዋም ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ይበ​ላል።”


በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፣ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፣ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos