Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ሕዝቤ፥ እኅ​ታ​ች​ሁ​ንም፦ ሥህ​ልት በሉ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ወንድሞቻችሁን ‘ሕዝቤ’፣ እኅቶቻችሁንም ‘ተወዳጆቼ’ ብላችሁ ጥሯቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የእስራኤልም ልጆች ቍጥር እንደማይሰፈርና እንዳማይቆጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እንዲሁም እነርሱ፦ “ሕዝቤ አይደላችሁም” በተባሉበት በዚያ ስፍራ፦ “የሕያው አምላክ ልጆች” ይባላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ስለዚህ ወንድሞቻችሁ የሆኑትን እስራኤላውያንን “አሚ” እኅቶቻችሁንም “ሩሃማ” ብላችሁ ጥሩአቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የእስራኤልም ልጆች ቍጥር እንደማይሰፈርና እንዳማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፥ እንዲህም ይሆናል፥ እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም ተብሎ በተነገረበት በዚያ ስፍራ የሕያው አምላክ ልጆች ይባላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 2:1
17 Referencias Cruzadas  

ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤


ከእ​ነ​ዚያ ወራት በኋላ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጋር የም​ገ​ባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሕጌን በል​ቡ​ና​ቸው አኖ​ራ​ለሁ፤ በል​ባ​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።


እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።


“ምድ​ራ​ቸው በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ በተ​ሠ​ራው በደል የተ​ሞ​ላች ብት​ሆ​ንም፥ እስ​ራ​ኤል መበ​ለት አል​ሆ​ነ​ችም፤ ይሁ​ዳም ከአ​ም​ላኩ ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አል​ራ​ቀም።


በት​እ​ዛ​ዜም ይሄዱ ዘንድ፥ ፍር​ዴ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ እነ​ርሱ ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል፥ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።


ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም አበ​ዛ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይበ​ዛሉ፤ ያፈ​ሩ​ማል፤ እንደ ጥን​ታ​ች​ሁም ሰዎ​ችን አኖ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቀድ​ሞም እንደ አደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ችሁ መል​ካም አደ​ር​ግ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋት ምድር ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ብም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ።


ማደ​ሪ​ያ​ዬም በላ​ያ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።


እና​ታ​ችሁ ሚስቴ አይ​ደ​ለ​ች​ምና፥ እኔም ባልዋ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና እና​ታ​ች​ሁን ተዋ​ቀ​ሱ​አት። ዝሙ​ቷን ከፊቷ፥ ምን​ዝ​ር​ና​ዋ​ንም ከጡ​ቶ​ችዋ መካ​ከል አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ።


በም​ድ​ርም ላይ ለእኔ እዘ​ራ​ታ​ለሁ፤ ይቅ​ርታ የሌ​ላ​ትን ይቅር እላ​ታ​ለሁ፤ ያል​ተ​ወ​ደ​ደች የነ​በ​ረ​ች​ውን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤም ያል​ሆ​ነ​ውን፥ “አንተ ሕዝቤ ነህ” እለ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጌታ​ዬና አም​ላኬ ነህ” ይለ​ኛል።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


ስለ​ዚህ እንደ ቸር​ነቱ የሰ​ጠን ይህ መል​እ​ክት አለ​ንና አን​ሰ​ለ​ችም።


አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፤


እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos