Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፣ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚለው፥ ዛሬ ድምፁን ስትሰሙት፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፦

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 3:7
27 Referencias Cruzadas  

“ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ እነ​ዚያ እንደ አሳ​ዘ​ኑት ጊዜ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ” ብሎ​አ​ልና።


ስሙኝ፤ ጎዳ​ና​ዬን ተከ​ተሉ፤ አድ​ም​ጡ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ትኖ​ራ​ለች፤ የታ​መ​ነ​ች​ዪ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ምሕ​ረት፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን ከእ​ና​ንተ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።


“ዛሬ ቃሉን ብት​ሰ​ሙት ልባ​ች​ሁን እል​ከኛ አታ​ድ​ርጉ፤” በፊት እንደ ተባለ ይህን ከሚ​ያ​ህል ዘመን በኋላ በዳ​ዊት ሲና​ገር፥ “ዛሬ” ብሎ አንድ ቀን እንደ ገና ይቀ​ጥ​ራል።


የእኔ የሆኑ በጎች ግን ቃሌን ይሰ​ሙ​ኛል፤ እኔም አው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይከ​ተ​ሉ​ኛል።


ዛሬ የሚ​ባ​ለው ቀን ሳለ ከእ​ና​ንተ ማንም ቢሆን ወደ ኀጢ​አት በሚ​ያ​ደ​ርስ ስሕ​ተት እን​ዳ​ይ​ጸና ሁል​ጊዜ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን መር​ምሩ።


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


ለእ​ርሱ በረ​ኛው ይከ​ፍ​ት​ለ​ታል፤ በጎ​ቹም ቃሉን ይሰ​ሙ​ታል፤ እር​ሱም በጎ​ቹን በየ​ስ​ማ​ቸው ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ አው​ጥ​ቶም ያሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋል።


“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ገ​ኝ​በት ጊዜ ፈል​ጉት፤ ቀር​ቦም ሳለ ጥሩት፤


ከዚህ ቦታ ያይ​ደሉ ሌሎች በጎ​ችም አሉኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ወደ​ዚህ አመ​ጣ​ቸው ዘንድ ይገ​ባ​ኛል፤ ቃሌ​ንም ይሰ​ሙ​ኛል፤ ለአ​ንድ እረ​ኛም አንድ መንጋ ይሆ​ናሉ።


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ተና​ገረ፤ ቃሉም በአ​ን​ደ​በቴ ላይ ነበረ።


ፊተ​ኛ​ይ​ቱም ድን​ኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድ​ስት የሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ገና እን​ዳ​ል​ተ​ገ​ለጠ መን​ፈስ ቅዱስ ያሳ​ያል።


እርሱም “እንኪያስ ዳዊት ‘ጌታ ጌታዬን “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤” አለው፤’ ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ባል​ተ​ስ​ማሙ ጊዜ ጳው​ሎስ አን​ዲት ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ ከእ​ርሱ ተመ​ለሱ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ አን​ደ​በት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ው​ነት እን​ዲህ ብሎ መል​ካም ነገር ተና​ግ​ሮ​አል።


ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ‘ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው አለ።’


“እና​ንተ ሰዎች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስሙ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ለያ​ዙት መሪ ስለ ሆና​ቸው ስለ ይሁዳ መን​ፈስ ቅዱስ አስ​ቀ​ድሞ በዳ​ዊት አፍ የተ​ና​ገ​ረው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ይገ​ባል።


መን​ፈስ ቅዱ​ስም ፊል​ጶ​ስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረ​ገላ ተከ​ተ​ለው” አለው።


መን​ፈስ ቅዱ​ስም ምስ​ክ​ራ​ችን ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios