Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 11:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 በደ​ረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በእ​ም​ነት ተሻ​ገ​ሩ​አት፤ የግ​ብፅ ሰዎች ግን ሲሞ​ክሩ ሰጠሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ሕዝቡ በደረቅ መሬት እንደሚኬድ ቀይ ባሕርን በእምነት ተሻገሩ፤ ግብጻውያን ግን እንደዚሁ ለማድረግ ሲሞክሩ ሰጠሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 በደረቅ ምድር እንደሚያልፉ የኤርትራን ባሕር በእምነት ተሻገሩ፤ የግብጽ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ሰመጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እስራኤላውያን በደረቅ ምድር እንደሚሻገሩ ሆነው ቀይ ባሕርን የተሻገሩት በእምነት ነው፤ ግብጻውያን ግን እንዲሁ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሁሉም ሰጠሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 በደረቅ ምድር እንደሚያልፉ በኤርትራ ባሕር በእምነት ተሻገሩ፥ የግብፅ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ተዋጡ።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 11:29
14 Referencias Cruzadas  

ከፊ​ታ​ቸ​ውም ባሕ​ሩን ከፈ​ልህ፤ በባ​ሕ​ሩም መካ​ከል በደ​ረቅ ዐለፉ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውን ግን ድን​ጋይ በጥ​ልቅ ውኃ እን​ዲ​ጣል በቀ​ላይ ውስጥ ጣል​ሃ​ቸው።


ምድር ፍሬ​ዋን ሰጠች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ይባ​ር​ከ​ናል፥ የም​ድ​ርም ዳርቻ ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።


እኛ ሕዝ​ብህ ግን፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ህም በጎች፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እና​መ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለን፤ ለልጅ ልጅም ምስ​ጋ​ና​ህን እን​ና​ገ​ራ​ለን።


ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “አት​ፍሩ፤ ዛሬ የም​ታ​ዩ​አ​ቸ​ውን ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ዩ​አ​ቸ​ው​ምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ ገቡ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


ሙሴም እጁን በባ​ሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ባሕ​ሩም ማለዳ ወደ መፍ​ሰሱ ተመ​ለሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በባ​ሕሩ መካ​ከል ጣላ​ቸው።


ከግ​ብፅ ምድር በወ​ጣ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረቀ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በነ​በ​ሩት፥ እና​ን​ተም ፈጽ​ማ​ችሁ ባጠ​ፋ​ች​ኋ​ቸው በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥ​ታት፥ በሴ​ዎ​ንና በዐግ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ሰም​ተ​ናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos