Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 መሠ​ረት ያላ​ትን ሠሪ​ዋና ፈጣ​ሪዋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆ​ነ​ላ​ትን ከተማ ደጅ ይጠኑ ነበ​ርና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ምክንያቱም መሠረት ያላትን፣ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ምክንያቱም መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህንንም ያደረገው ጽኑ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር ያቀዳትንና የሠራትን ከተማ ይጠባበቅ ስለ ነበር ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 11:10
11 Referencias Cruzadas  

በዚህ የሚ​ኖር ከተማ ያለን አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​መ​ጣ​ውን እን​ሻ​ለን እንጂ።


እኛስ ሀገ​ራ​ችን በሰ​ማይ ያለ​ችው ናት፤ ከዚ​ያም እር​ሱን ጌታ​ችን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ጠ​ባ​በ​ቃ​ለን።


እና​ንተ ግን፥ የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰ​ማ​ያት ወደ አለ​ችው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ደስ ብሎ​አ​ቸው ወደ​ሚ​ኖሩ አእ​ላፍ መላ​እ​ክ​ትም ደር​ሳ​ች​ኋል።


በም​ድር ያለው ማደ​ሪያ ቤታ​ችን ቢፈ​ር​ስም፥ በሰ​ማይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰው እጅ ያል​ሠ​ራው ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ቤት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን።


ቤትን ሁሉ ሰው ይሠ​ራ​ዋ​ልና፤ ለሁሉ ግን ሠሪው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


በአ​ባቴ ቤት ብዙ ማደ​ሪ​ያና ማረ​ፊያ አለ፤ እን​ዲ​ህስ ባይ​ሆን ኖሮ ቦታ ላዘ​ጋ​ጅ​ላ​ችሁ እሄ​ዳ​ለሁ እላ​ችሁ ነበር።


ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።


ስለ​ዚህ የማ​ይ​ና​ወጥ መን​ግ​ሥ​ትን ስለ​ም​ን​ቀ​በል በማ​ክ​በ​ርና በፍ​ር​ሀት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ እያ​ሰ​ኘን የም​ና​መ​ል​ክ​በ​ትን ጸጋ እን​ያዝ።


የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ምን ይመ​ል​ሳሉ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መሠ​ረ​ታት፤ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ሕዝብ አዳ​ና​ቸው።


አሁን ግን፥ በሰ​ማ​ያት ያለ​ች​ውን የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሀገር ተስፋ ያደ​ርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ አያ​ፍ​ርም፤ ተስፋ ያደ​ረ​ጉ​አ​ትን ሀገር አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios