Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 10:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በሥ​ጋው መጋ​ረጃ በኩል የሕ​ይ​ወ​ት​ንና የጽ​ድ​ቅን መን​ገድ ፈጽሞ አድ​ሶ​ል​ና​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይኸውም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል በከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በአዲስና በሕያው መንገድ በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል ተከፍቶልን፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የምንገባውም በመጋረጃው፥ ማለትም በሥጋው አማካይነት በከፈተልን በአዲሱና ሕያው በሆነው መንገድ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 10:20
20 Referencias Cruzadas  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።


እው​ነ​ተ​ኛዉ የበ​ጎች በር እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩ​ልም የሚ​ገባ ይድ​ናል፤ ይገ​ባ​ልም ይወ​ጣ​ልም፤ መሰ​ማ​ር​ያም ያገ​ኛል።


ከሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ በስ​ተ​ኋላ የነ​በ​ረ​ች​ውን የው​ስ​ጠ​ኛ​ዪ​ቱን ድን​ኳን ግን ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ይሉ​አት ነበር።


ፊተ​ኛ​ይ​ቱም ድን​ኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድ​ስት የሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ገና እን​ዳ​ል​ተ​ገ​ለጠ መን​ፈስ ቅዱስ ያሳ​ያል።


ይህ​ችም ተስፋ ነፍ​ሳ​ችን እን​ዳ​ት​ነ​ዋ​ወጥ እንደ መል​ሕቅ የም​ታ​ጸና ናት፤


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የበ​ጎች በር እኔ ነኝ።


የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥


ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


ፀሐ​ዩም በጨ​ለመ ጊዜ የቤተ መቅ​ደሱ መጋ​ረጃ ከላይ እስከ ታች ከመ​ካ​ከሉ ተቀ​ደደ።


የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ።


እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤ ምድርም ተናወጠች፤ ዐለቶችም ተሰነጠቁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስ​ር​የቱ መክ​ደኛ ላይ በደ​መ​ናው ውስጥ እታ​ያ​ለ​ሁና እን​ዳ​ይ​ሞት በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ወዳ​ለው ወደ ስር​የቱ መክ​ደኛ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ሁል​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ገባ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን ንገ​ረው።


ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና፤ እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።


ሁለ​ቱ​ንም አድሶ አንድ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ በሥ​ር​ዐቱ የት​እ​ዛ​ዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕር​ቅ​ንም አደ​ረገ።


ነገር ግን ነው​ረኛ ነውና መቅ​ደ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​ረ​ክስ ወደ መጋ​ረ​ጃው አይ​ግባ፤ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም አይ​ቅ​ረብ፤ የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸው እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”


“ስለ ሕዝ​ቡም ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ያር​ዳል፤ ደሙ​ንም ወደ መጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም ደም እን​ዳ​ደ​ረገ በፍ​የሉ ደም ያደ​ር​ጋል፤ በመ​ክ​ደ​ኛው ላይና በመ​ክ​ደ​ኛው ፊት ይረ​ጨ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios