Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነ​ርሱ ያል​ፋሉ፤ አንተ ግን ትኖ​ራ​ለህ፤ ሁሉ እንደ ልብስ ያረ​ጃል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እነርሱ ሁሉ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ እነርሱ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 1:11
22 Referencias Cruzadas  

ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁን ወደ ሰማይ አንሡ፤ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመ​ል​ከቱ፤ ሰማ​ያት እንደ ጢስ በን​ነው ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ርም እንደ ልብስ ታረ​ጃ​ለች፤ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እን​ዲሁ ይሞ​ታሉ፤ ማዳ​ኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ናት፤ ጽድ​ቄም አታ​ል​ቅም።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ሰማ​ያት እንደ መጽ​ሐፍ ጥቅ​ልል ይጠ​ቀ​ለ​ላሉ፤ ከወ​ይ​ንና ከበ​ለ​ስም ቅጠል እን​ደ​ሚ​ረ​ግፍ ከዋ​ክ​ብት ሁሉ ይረ​ግ​ፋሉ።


አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፤ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደ ፊት የለም።


ሰማ​ይና ምድር ያል​ፋል፤ ቃሌ ግን አያ​ል​ፍም።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


አንድ ጊዜ ደግሞ ያለ​ውም ፍጡ​ራን ናቸ​ውና፥ የማ​ይ​ና​ወ​ጠው ይኖር ዘንድ፥ የሚ​ና​ወ​ጠ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ያሳ​ያል።


“እነሆ፥ አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር ይሆ​ና​ልና፤ የቀ​ደ​ሙ​ትም አይ​ታ​ሰ​ቡም፤ ወደ ልብም አይ​ገ​ቡም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “አንተ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አም​ባዬ ነህ፤ አም​ላ​ኬና ረዳቴ ነው፥ በእ​ር​ሱም እታ​መ​ና​ለሁ” ይለ​ዋል።


ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


“በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦


እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።


እነሆ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፤ ማን ይጎ​ዳ​ኛል? እነሆ፥ ሁላ​ችሁ እንደ ልብስ ታረ​ጃ​ላ​ችሁ፤ ብልም ይበ​ላ​ች​ኋል።


ይህን የሠ​ራና ያደ​ረገ፥ ትው​ል​ድ​ንም ከጥ​ንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው እኔ ነኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ፥ ይቅ​ርም አለኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ሆነኝ።


እንደ ልብስ ፈጥ​ነው ያረ​ጃ​ሉና አይ​ቈ​ዩም፤ ብል እንደ በላ​ውም ይሆ​ናሉ፤ ጽድቄ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ማዳ​ኔም ለልጅ ልጅ ይሆ​ናል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።


አዲስ ትእ​ዛዝ በማ​ለቱ የቀ​ደ​መ​ች​ቱን አስ​ረ​ጃት፤ አሮ​ጌና ውራጅ የሆ​ነ​ውስ ለጥ​ፋት የቀ​ረበ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios