Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐጌ 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፣ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ወደ ተራራ ውጡ፤ ዕንጨት አምጡ፤ ቤቱን ሥሩ፤ እኔም በርሱ ደስ ይለኛል፤ እከበርበታለሁም” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በእርሱ ደስ እንዲለኝና እንድከበርበት፥ ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትን አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ። ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በሉ አሁን ወደ ኰረብቶች ውጡ፤ እንጨትም ቈርጣችሁ አምጡ፤ ቤተ መቅደሱን እንደገና አድሳችሁ ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ብሎኝ እመሰገንበታለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፥ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ሐጌ 1:8
21 Referencias Cruzadas  

ለጠ​ራ​ቢ​ዎ​ችና ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችም ብር ሰጡ፤ የፋ​ር​ስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀ​ደ​ላ​ቸው የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ በባ​ሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲ​ዶ​ናና ለጢ​ሮስ ሰዎች መብ​ልና መጠጥ፥ ዘይ​ትም ሰጡ።


አሁ​ንም ስሜ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መር​ጫ​ለሁ፤ ቀድ​ሻ​ለ​ሁም፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም ዘወ​ትር በዚያ ይሆ​ናሉ።


አሕዛብን ሁሉ አናውጣለሁ፥ በአሕዛብ ሁሉ የተመረጠውም ዕቃ ይመጣል፣ ይህንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “በፊቴ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ጸሎ​ት​ህ​ንና ልመ​ና​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እንደ ጸሎ​ት​ህም ሁሉ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠ​ራ​ኸ​ውን ቤት ቀድ​ሻ​ለሁ፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም በዘ​መኑ ሁሉ በዚያ ይሆ​ናሉ።


በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አዝ​ዛ​ለሁ፤ በክ​ብ​ሬም እቀ​ደ​ሳ​ለሁ።


ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ትጠቡ ዘንድ ከማ​ጽ​ና​ና​ቷም ጡት ትጠ​ግቡ ዘንድ እጅግ ጠጥ​ታ​ችሁ በክ​ብ​ርዋ ሙላት ደስ ይላ​ችሁ ዘንድ።


የመ​ቅ​ደ​ሴ​ንም ስፍራ ያከ​ብሩ ዘንድ የሊ​ባ​ኖስ ክብር፥ ጥዱና አስ​ታው፥ ባር​ሰ​ነ​ቱም ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፥


የቄ​ዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ የነ​ባ​ዮ​ትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይም የተ​መ​ረ​ጠው መሥ​ዋ​ዕት ይቀ​ር​ባል፤ የጸ​ሎቴ ቤትም ይከ​ብ​ራል።


በሦ​ስት ተራ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ፥ በአ​ንድ ተራ እን​ጨት ይደ​ረግ፤ ወጭ​ውም ከን​ጉሡ ቤት ይሰጥ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማ​ንያ አራት ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎ​ሞን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚ​ባ​ለው በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመረ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።


አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ልጉ ዘንድ ልባ​ች​ሁ​ንና ነፍ​ሳ​ች​ሁን ስጡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ወደ​ሚ​ሠ​ራው ቤት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦ​ትና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንዋየ ቅድ​ሳት ታመጡ ዘንድ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ ሥሩ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios