Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 41:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ደግ​ሞም ተኛ፤ ሁለ​ተኛ ሕል​ም​ንም አየ፤ እነ​ሆም፥ በአ​ንድ አገዳ ላይ የነ​በሩ፥ ያማ​ሩና ምርጥ የሆኑ ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ፈርዖንም እንደ ገና እንቅልፍ ወስዶት ሳለ፣ ሌላ ሕልም አየ። በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ፣ ፍሬአቸው የተንዠረገገና ያማረ ሰባት የእሸት ዛላዎች ሲወጡ አየ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ፈርዖንም እንደገና እንቅልፍ ወስዶት ሳለ፥ ሌላ ሕልም አየ። በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ፥ ፍሬያቸው የተንዠረገገና ያማረ ሰባት የእሸት ዛላዎች ሲወጡ አየ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ተመልሶም እንቅልፍ በወሰደው ጊዜ እንደገና ሌላ ሕልም አየ፤ በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች አየ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ደግሞም ተኛ ሁለተኛም ሕልምን አየ እነሆም በአንድ አገዳ ላይ የነበሩ ያማሩና መልካም የሆኑ ሰባት እሸቶች ወጡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 41:5
4 Referencias Cruzadas  

ሁለ​ቱም በአ​ን​ዲት ሌሊት ሕል​ምን አለሙ። በግ​ዞት ቤት የነ​በ​ሩት የግ​ብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ ሁለ​ቱም እየ​ራ​ሳ​ቸው ሕል​ምን አለሙ።


መል​ካ​ቸው የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ እነ​ዚያ ሰባት ላሞች መል​ካ​ቸው ያማ​ረ​ውን፥ ሥጋ​ቸ​ውም የወ​ፈ​ረ​ውን ሰባ​ቱን ላሞች ዋጡ​አ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም ነቃ፤


እነ​ሆም፥ ከእ​ነ​ርሱ በኋላ የሰ​ለ​ቱና በነ​ፋስ የተ​መቱ ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤


በላሙ ቅቤ፥ በበ​ጉም ወተት፥ ከፍ​የል ጠቦ​ትና ከላም፥ ከጊ​ደ​ሮ​ችና ከበ​ጎች ስብ ጋር፥ ከፍ​ትግ ስንዴ ጋር መገ​ባ​ቸው፤ የዘ​ለ​ላ​ው​ንም ደም የወ​ይን ጠጅ አድ​ር​ገው ጠጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos