Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 26:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አባ​ትህ አብ​ር​ሃም ቃሌን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ፍር​ዴን፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ሕጌ​ንም ጠብ​ቆ​አ​ልና።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ይኸውም አብርሃም ቃሌን ሰምቶ፣ ድንጋጌዬን፣ ትእዛዜን፣ ሥርዐቴንና ሕጌን በመጠበቁ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አንተን የምባርክበትም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁትን ትእዛዞች፥ ድንጋጌዎችንና ሕጎችን ሁሉ ስለ ጠበቀ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴም ሕጌ፥ ጠብቆአልና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 26:5
14 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረው ሄደ፤ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ፤ አብ​ራ​ምም ከካ​ራን በወጣ ጊዜ ሰባ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ።


አብ​ር​ሃ​ምም ልጁን ይስ​ማ​ኤ​ልን፥ በቤ​ቱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን ሁሉ፥ በወ​ር​ቅም የገ​ዛ​ውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወን​ዶ​ቹን ሁሉ ወሰደ። የሥ​ጋ​ቸ​ው​ንም ቍል​ፈት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ለው በዚ​ያው ቀን ገረዘ።


ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ለም​ት​ወ​ድ​ደው ልጅ​ህም ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ምና መባ​ረ​ክን እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤


የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉም በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤ ቃሌን ሰም​ተ​ሃ​ልና።”


ይስ​ሐ​ቅም በጌ​ራራ ተቀ​መጠ። የዚ​ያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ስለ ርብቃ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “እኅቴ ናት” አላ​ቸው፤


እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።


“ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና።


አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ።


አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos